ሰንበት ትምህርት ቤት
ፈለገ ህይወት
ኆኅተ ምስራቅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት

Addis Ababa Diocess Sunday Schools Unity
ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት ትምህርት ቤት ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት …

Head Office
Addis Ababa Diocess Sunday Schools Unity
01 • አራዳ • አዲስ አበባ
Website Directory
የድር ጣቢያ አርማዎችን እና የቤተ ክርስቲያን ስሞችን ይመልከቱ እና በቀጥታ ወደ ገጹ ይግቡ።
አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በትምህርተ ሃይማኖት፣ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያና በዓለም የክርስትና ታሪክ፣ በቤተክርስቲያን የአብነት ትምህርቶች፣ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ምስጢራዊ አፈጻጸም ፣በተቀደሰ ትውፊት ላይ ወጥነትና ተከታታይነት ያለው እውቀትን ማስተላለፍ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን በተለይም ሕፃናት አዳጊዎችን እና ወጣቶች በነገረ ሃይማኖት ልቀው፣ የተመሟላ ስብእና ይዘው አርአያነት ያላቸው ጉልህ ሃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ድርሻ የሚወስዱ፣ አባቶቻቸውን የሚተኩ፣ እና በሀገራዊ ሆነ በዓለም አቀፋዊ የለውጥ ክስተቶች ላይ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ብቁ ትውልድ ሆነው ማየት

እግዚአብሔርን መፍራት ፣ ሰውን ማክበር ፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት ፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ ፣ ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣ ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
Addis Ababa Diocess Sunday Schools Unity
ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት ትምህርት ቤት ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት ስታካሒድ ኖራለች፤ በተለይም ደግሞ በትምህርት ዘርፍ ወጣቱን ከሕፃንነቱ ጀምሮ በማስተማር ለሰው ልጅ በሚያፈልጉት የአአምሮና የመንፈስ እድገት የተሟላ እንዲሆኑ ስትሠራ ቆይታለች፤ ወደፊትም ትሠራለች::

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
+251941411269
info@eotcssu.et
Active
01 • አራዳ • አዲስ አበባ
አካባቢ