Sunday SchoolActive

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም

E.O.T.C Addis Abeba Diocese Debre Tabor St/Michael and Tadeku Abune TakleHaimanot Monastery

የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ደብረ ታቦር ሰንበት ትምህርት ቤት

ሰንበት ት/ቤታችን በአሁኑ ስዓት በቃለዓዋዲው የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በመዋቅር ተደራጅታ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በዚህም የስራ አመራር፤ የስራ አስፈፃሚ እና በኦዲትና ኢንስፔክሽን ስር ክፍሎችን አዋቅሮ አባላት በክፍሎች በማሳተፍ  እየሰራች ትገኛል። ስርዓተ ትምህርቱንም አዲስ በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት መሰረት አባላትን ከሕፃናት ጅምሮ በመቀበል  እንዲሁም የ

7 • ጉለሌ • አዲስ አበባ
1992 ዓ.ም
+251908395741
E.O.T.C Addis Abeba Diocese Debre Tabor St/Michael  and Tadeku Abune TakleHaimanot Monastery
E.O.T.C Addis Abeba Diocese Debre Tabor St/Michael  and Tadeku Abune TakleHaimanot Monastery

Sunday School

E.O.T.C Addis Abeba Diocese Debre Tabor St/Michael and Tadeku Abune TakleHaimanot Monastery

7 • ጉለሌ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

የቤተ ክርስቲያን ዶግማ ፣ቀኖናና ትውፊት ሳይለወጥ ሳይበረዝ በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ፡፡
ትውልዱን ከቤተክርስቲያኒቷ የማንነት መገለጫ አስተምህሮዎች የሚያስወጡ የየዘመናቱን ኢ-ክርስቲያናዊ ለውጦች በመከታተል በመቅረጽ ጠንካራ የማሕበራዊ ሕይወት እና ኃላፊነቱን የሚወጣ፣ታማኝ አገልጋይ ፣ በጎ አርዓያነት ያለው ትውልድ ማፍራት፡፡

የእኛ ራእይ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን በተለይም ሕፃናት አዳጊዎችን እና ወጣቶች በነገረ ሃይማኖት ልቀው፣ የተመሟላ ስብእና ይዘው አርአያነት ያላቸው ጉልህ ሃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ድርሻ የሚወስዱ፣ አባቶቻቸውን የሚተኩ፣ እና በሀገራዊ ሆነ በዓለም አቀፋዊ የለውጥ ክስተቶች ላይ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ብቁ  ትውልድ ሆነው ማየት

የእኛ እሴቶች

* ፈሪሐ እግዚአበሔር

*  ዘመኑን መዋጀት

* በሃይማኖት መኖር

* በፍቅር ማገልገል

* ቁርጠኝነት

* በጎ አርዓያ መሆን

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም

የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ደብረ ታቦር ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

የደብረ ታቦር ሰንበት ትምህረት ቤት አመሰራረት   የገዳማችንን የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ምስረታ ተከትሎ የመቃኞ ቤቱ ግንባታ በተጀመረበት ቀን ጥቅምት 12 1992 ዓ.ም መንፈሳዊ ኣላማ ባላቸው መንፈስ ቅዱስ ባስባበስባቸው በአጥቢያው በሚኖሩ ወጣቶች እና ህፃናት ሰንበት ትምህርት ቤቱ ተመሰረተ፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ስያሜ የመጣውም ከገዳሙ ስያሜ መሰረት በማድረግ እና ገዳሙ የተመሰረተበት ተራራማ አካባቢ በመነሳት ነው፡፡

ስለ እኛ

ሰንበት ት/ቤታችን በአሁኑ ስዓት በቃለዓዋዲው የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በመዋቅር ተደራጅታ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በዚህም የስራ አመራር፤ የስራ አስፈፃሚ እና በኦዲትና ኢንስፔክሽን ስር ክፍሎችን አዋቅሮ አባላት በክፍሎች በማሳተፍ  እየሰራች ትገኛል።

ስርዓተ ትምህርቱንም አዲስ በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት መሰረት አባላትን ከሕፃናት ጅምሮ በመቀበል  እንዲሁም የተለያዩ ጉባኤ በመዘርጋት እና በማስተማር እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን በማገልገል ላይ ትገኛለች።

በአጠቃላይ በእነዚህ ክፍሎች አባላቱን አደራጅቶ እየሰራች ስትገኝ ክፍሎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከሩ የመጡ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ያጋጠሙ ፈተናዎችንም እያለፈች በእግዚአብሔር አብ ፈቃድ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

የገዳሙ መጠሪያ  ስም ስያሜ

አንድ ቦታ ሲመሰረትም ሆነ ሲሰየም አባቶቻችን መጽሐፍ ቅዱስን እና ታሪክን መሰረት ያደረገ ስያሜ አውጥተው ደብር(ገዳም) ያቋቁማሉ። "የገዳማችንን የስም ስያሜ አመጣጥ" ከዚህ በታች እናያለን
የአጥቢያው  ምዕመናን በጊዜው በትላልቅ አድባራት አና ደብራት የተከበቡ ቢሆንም ፍላጎታቸው በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሰረት እና ለስራ መነሳሳቱ በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን የማጣት ሳይሆን አሰቀድሞ የነበረውን የቦታውን ክብር እና ስም የመመለስ ዓላማ ስለነበር ቀድሞ የቦታው መጠሪ  ስም  "መንበረክብር" ስለነበር ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል;;
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን ክብሩን በገለጠበት እና ሃዋርያትን "የሰውንልጅሰዎችማንይሉታል "  (በማቴ.16፥13)  ብሎ ለጠየቃቸው  ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ወደ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል።ይህ ተራራ ደብረ ታቦር (የታቦር ተራራ) ይባላል። ይህም ተራራ መልክአ ምድራዊ አቀማመጡ እግዚአብሔር አምላክ ብርሃነ መለኮቱን ከገለጠበት ከደብረ ታቦር ተራራ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው በጊዜው በነበሩት የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ጳውሎስ   "ደብረታቦር" ተብሎ እንዲጠራ ሰይመውታል።      በዚህ መሰረት የገዳሙ መጠሪያ  “መንበረ ክብር ደብረ ታቦር የቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትገዳም”’ ተብሏል፡፡

በገዳሙ ያሉ ታቦታት ታሪክ

በገዳሙ የሚገኙ ታቦታት ፮ ሲሆኑ እነርሱም የቅዱስ ሚካኤል ፣የአቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የቅዱስት ክርሰቶስ ሰምራ ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅድስት አርሴማ ታቦታት ይገኛሉ።ወደ ገዳሙ ታቦታቱ የገቡበትን  ጊዜያት ከዚህ በታች እናያለን
1.የቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ታቦት ግንቦት 11 /1992 ዓ.ም
2.የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ታቦት  ግንቦት 11 /1994 ዓ.ም
3.የእግዚአብሔር ወልድ ታቦት መጋቢት 28/1996 ዓ.ም
4.የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም  ህዳር 21 /1998 ዓ.ም
5.የቅድስት አርሴማ ጳግሜ 1 /2003 ዓ.ም

በገዳሙ የሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት

✨ መስከረም 29 ቀን የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል
✨ ህዳር 12 የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በአል
✨ ህዳር 21 በዓለ ጽዮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
✨ ታህሳስ 6 ቀን የቅድስት አርሴማ ፍልሰተ ስጋ
✨ ታህሳስ24 የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ልደት
✨ ጥር 12 ቃና ዘገሊላ
✨ መጋቢት 29 የእግዚአብሔር ወልድ (ፅንሰቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ )
✨ ግንቦት 12  የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዓመታዊ ክብረ በአል
- የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አፅሙ
- የገዳሙ ቅዳሴ ቤት
✨ ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል
✨ ነሐሴ 24 የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት

የገዳሙ የጠበል ስፍራ

የገዳሙ የጠበል ስፍራ በቅዱስ ሚካኤል ድንቅ ታምር በቤተክርስቲያኑ አቅራቢ ፈልቆ የካቲት 14 1994 ዓ.ም ተመሠረተ። በውስጡም የቅዱስ ሚካኤል ጠበል፣የአቡነ ተክለሃይማኖት፣የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም፣የቅድስት አርሴማ ጠበል ይገኛሉ። ቦታው ብዙ ታምራት ታይቶበታል ፤ ከልዩ ልዩ በሽታም ብዙዎች ድነዋል።
✨ በየአመቱ  ህዳር 21   በጽዮን በዓል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ታቦተ ህግ ወደ ጠበል ስፍራው በመውረድ ቦታውን ይባርካል።

የመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ምስረታ ታሪከ

ገዳሙ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር ካሉ ገዳማት አንዱ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ሰሜናዊ ክልል ከመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት  6 ኪ.ሜ  ርቀት  ላይ የሚገኝ ያማረ መልክዓ  ምድራዊ አቀማመጥ ባለው በእድሜ ጠገብ እፅዋት በተከበበ ተራራ ጉብታ ላይ የተገደመ ታሪካዊ ገዳም ነው።

የገዳሙ ጥንተ ታሪክ

ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ቤተ መንግስታቸውን እንጦጦ ላይ መገንባታቸውን ተከትሎ ይህ ስፍራ(የአሁኑ መንበረ ክብር) ለተለያዩ አገልግሎቶች ተጠቅመውበታል።በአድዋ ጦርነት የክተት አዋጅ መታወጁን ተከትሎ የሐረር ክፍለ ሀገር ገዢ የነበሩት ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል  በመያዝ ዝግጅት ሲያደርጉበት የነበረ ስፍራ ነው።እንዲሁም ለጦርነቱ የሚሆኑ የጦር መሳሪያዎች ይመረቱበት የነበረ ታሪካዊ ቦታ ነው።ከጦርነቱ ድል በኋላ ቦታው ለልዑል ራስ መኮንን በእርስትነት አጼ ሚኒሊክ ተሰጥቷቸዋል።

ቦታው ያማረ መልክዓ ምድር ያለው በመሆኑ የመናንያን እና የመነኮሳት  ቦታ ሆኖ እንደነበረ ታሪክ ይነግረናል።በዚህ ስፍራ   አባ አየለ የተባሉ መነኩሴ ማረፊያ የሳር ክዳን ሰርተው ስብሃተ እግዚአብሔር ያደርሱ ነበር።

አፄ ምኒልክ  እና ራስ መኮንን ቦታውን ይወዱት ስለነበረ ጥር 27 በ1889 ዓ.ም በመድኃኔዓለም ዕለት ለተወለዱት ለልጅ ኢያሱ ልደት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ አፄ ምኒልክ ከእስራኤል ታቦተ መድኃኔዓለምን አስመጥተው የአባ አየለ የሳር ክዳን ቤት ታድሶ በረንዳ ተሰርቶለት በሀምሌ ወር በ1903 በመቃኞ ቤቱ ታቦተ ሕጉ እንዲገባ አድርገዋል ።ሐምሌ 27 ማህሌት ተቆሞ የቅዳሴ ስርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ በአቡነ ማቴዎስና በእጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ ተመርቆ የመድኃኔዓለም በዓል ተከብሯል።

በቀጣዩ አመትም ጥቅምት 27 በ1904 ዓ.ም የመድኃኔዓለም ንግስ በአል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል ለዚህም በዓል ክብር ነጋሪት  ተመቷል መድፍም ተተኩሷል ።በዚሁ አመት ባልታወቀ የእሳት ቃጠሎ የመቃኞ ቤቱ ይቃጠላል በፈቃደ እግዚአብሔር የመድኃኔዓለም ታቦት ሳይቃጠል በመትረፉ ታቦተ መድኃኔዓለም ከዚህ ስፍራ በመነሳት አሁን ወደሚገኝበት ቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሊያርፍ ችሏል።

የገዳሙ አመሰራረት

በመልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ከልምላሜ ጋር ያሸበረቀው ይህ ስፍራ ከ88 ዓመታት በኃላ በመስከረም 16 1992ዓ.ም በመስቀል ደመራ በአል ዕለት ምዕመናን በመካከላቸው ለቦታው ልዩ ፍቅር ባላቸው አባት ቆሞስ አባ ሀይለ ገብርኤል መሪ በማድረግ በቦታው ደመራን በመለኮስ ብርሃን የሆነ እርሱን የብርሃን አምላክ በማመስገን ከአጥቢያው ምዕመናን ጋር በአንድነት ሆነው መስቀልን ያከበሩበት በዓል ለገዳሙ ምስረታ ሂደት ጅማሮ ለልዩ ቀን ነበር።

በህዝቡ  ታላቅ ፍላጎት እና ተነሳሽነት በአባታችን ቆሞስ አባ ሀይለ ገብርኤል አሰባሳቢነት እና አባታዊ መጋቢነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የቤተ ክህነትና የከተማ መስተዳድር ፍቃድ በማግኘት  በ1992 ዓ.ም ጥቅምት 12 ቀን ብዙ ምዕመናን በተሰበሰቡበት የቤተክርስቲያን ምስረታ የመቃኞ ቤቱ ግንባት በይፋ ተጀመረ።

5825789551665334543.jpg 155.81 KBግንቦት 12 ቀን 1992 ዓ.ም ከሰባት ወራት በኋላ መቃኞ ቤቱ ተጠናቆ በታላቅ ድምቀት ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።በዚሁ አመት ሰኔ 8 ቀን በአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ  ሊቃነ ጳጳሳትን በማስከተል ገዳሙ አሁን የሚጠቀምበትን ህንፃ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኑረው ቦታውንም ባርከዋል።

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251908395741

ኢሜል

debretabor24@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

7 • ጉለሌ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

E.O.T.C Addis Abeba Diocese Debre Tabor St/Michael and Tadeku Abune TakleHaimanot Monastery

Address

7 • ጉለሌ • አዲስ አበባ

Lat 9.07087Lng 38.74394
Open in Google Maps