
የካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን
Kara Kore Mezgebe Mhiret KIdus Fanuel Church
ወንድሞች በብረት ቢሆኑ እነሆ ያማረ የተዋበም ነው። መዝ፡፻፴፪፥፩


Sunday School
Kara Kore Mezgebe Mhiret KIdus Fanuel Church
11 • Kolfe Keranio • Addis Ababa
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
የካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።
<p> ስለ ሃይማኖታቸው በቂ እውቀት ያላቸው አባላት እና የነገይቱ ቤተክርስቲያን ተተኪ አገልጋዮችን ማፍራት፡፡ </p>
<p>የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን እምነትና ስርዓት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጣቱን ትውልድ አደራጅቶ ሰማያዊ ርስት የሚወርስበትን ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም እንዲዳረስ ማድረግ፤ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ ቀኖና እና ትውፊት ጠብቆ እና አስጠብቆ በአበው እግር ተተኪ እንዲሆን ማድረግ፤ የቤተክርስቲያን ልጆችን በቀደመች እምነታቸው እንዲጸኑ ማስቻል ነው፡፡</p>
<p>ቅዱስና ምሳሌ የሆነ አገልግሎት ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት፣ ዘመኑን መቅደም ፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነት</p>
ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
የካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን
ሐመረ ኖኅ ሰንበት ትምህርት ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
ወንድሞች በብረት ቢሆኑ እነሆ ያማረ የተዋበም ነው። መዝ፡፻፴፪፥፩

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
በአህዛብ የተከበበው መንደራቸውና መንፈሳዊት ማዕድን የተጠማች ነፍሳቸው እረፍት የነሷቸው የወታደር ሰፈር ምዕመናን ነፍሳቸውን ወደ ሕይወት ምንጭ ታደርሳቸው ዘንድ ሐመረ ኖኅ የተሰኘች የጸሎት ማህበር መሰረቱ። የአከባቢው ምዕመናን በአከባቢያቸው ቤ/ን ለማስተከል በ1989 ዓ.ም አሁን መስቀል ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ የቅዱስ ፋኑኤልን ቤ/ን አንጸው ጽላት እስከማስገባትና ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና ምዕመናንን ለምረቃ እስከመጥራት ደርሰው በአህዛብና በጸጥታ ኃይሎች ሰፍራው ተከቦና ለማለፍ ተከልክለው ፤ በሚይሳዝንም ሁኔታ ቤ/ኗ በዶዘር እስከመፍረስ በመድረሱ ፈቃደ እግዚአብሔር ሳይሆን ቀርቶ ፈርሶ የነበረውን ቤ/ን በማኅበሩ አባላት በተነሳ በጊዜው ብዙ ዋጋ በመክፈልና በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር 9 1993 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው የቅዱስ ፋኑኤልን ታቦት አስገቡ።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
+251911223344
ኢሜል
hamer.nohe03@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
11 • Kolfe Keranio • Addis Ababa
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ