
ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል
DEBRE SINA KIDUS EGIZIABHER AB CATHEDRAL
ሰንበት ት/ቤታችን በአሁኑ ስዓት በቃለዓዋዲው የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በመዋቅር ተደራጅታ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በዚህም የስራ አመራር፤ የስራ አስፈፃሚ እና በኦዲትና ኢንስፔክሽን ስር ክፍሎችን አዋቅሮ አባላት በክፍሎች በማሳተፍ እየሰራች ትገኛል። ስርዓተ ትምህርቱንም አዲስ በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት መሰረት 1- 12 ክፍል አባላትን ከሕፃናት ጅምሮ በመቀ…


Sunday School
DEBRE SINA KIDUS EGIZIABHER AB CATHEDRAL
07 • ጉለሌ • አዲስ አበባ
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።
<p> በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በትምህርተ ሃይማኖት፣ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያና በዓለም የክርስትና ታሪክ፣ በቤተክርስቲያን የአብነት ትምህርቶች፣ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ምስጢራዊ አፈጻጸም ፣በተቀደሰ ትውፊት ላይ ወጥነትና ተከታታይነት ያለው እውቀትን ማስተላለፍ </p>
<p> የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን በተለይም ሕፃናት አዳጊዎችን እና ወጣቶች በነገረ ሃይማኖት ልቀው፣ የተመሟላ ስብእና ይዘው አርአያነት ያላቸው ጉልህ ሃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ድርሻ የሚወስዱ፣ አባቶቻቸውን የሚተኩ፣ እና በሀገራዊ ሆነ በዓለም አቀፋዊ የለውጥ ክስተቶች ላይ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ብቁ ትውልድ ሆነው ማየት </p>
<p> እግዚአብሔርን መፍራት ፣ ሰውን ማክበር ፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት ፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ ፣ ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣ ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት </p>
ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል
ዕፀ ጳጦስ ሰንበት ትምህርት ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
ሰንበት ት/ቤታችን በአሁኑ ስዓት በቃለዓዋዲው የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በመዋቅር ተደራጅታ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በዚህም የስራ አመራር፤ የስራ አስፈፃሚ እና በኦዲትና ኢንስፔክሽን ስር ክፍሎችን አዋቅሮ አባላት በክፍሎች በማሳተፍ እየሰራች ትገኛል።
ስርዓተ ትምህርቱንም አዲስ በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት መሰረት 1- 12 ክፍል አባላትን ከሕፃናት ጅምሮ በመቀበል እንዲሁም የተለያዩ ጉባኤ በመዘርጋት እና በማስተማር እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን በማገልገል ላይ ትገኛለች።
በአጠቃላይ በእነዚህ ክፍሎች አባላቱን አደራጅቶ እየሰራች ስትገኝ ክፍሎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከሩ የመጡ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ያጋጠሙ ፈተናዎችንም እያለፈች በእግዚአብሔር አብ ፈቃድ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
የመቃኞ ቤተክርስቲያኑ ሥራ መጠናቅን ተከትሎ የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ጽላት የሚመጣው ከደብረ ሰላም ቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ነበርና ኮሚቴው ታቦተ ሕጉ መጥቶ እንደሚገባ ቀድመው ለምዕመናኑ አስተዋውቀው ስለነበር ሐምሌ 30/1969ዓም
በጉጉት እየተጠባበቁ እያሉ ፓትርያርኩ በዕለቱ ቀድሞ የተያዘ መርሐ ግብር ስለነበራቸው በጣም አዝነው በዋዜማው ሐምሌ 29/ 1969ዓም ከሰዓት በኃላ መጥቼ ቤተክርስቲያኑን ባርኬ ታቦቱን ላስገባ ብለው በቃላቸው መሰረት ሐምሌ 29/ 1969ዓም ከሰዓት በኋላ ከብፁዓን አባቶች ጋር በመሆን ወደ ቀድሞው ወልደማርያም ጫካ የአሁኑ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ፡፡
ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ወደ ቤተክርስቲያን የሚያስገባው መንገድ መኪና የሚያሳልፍ ስላልነበረ መኪናዎቹ ቆመው ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን አባቶች በእግር ወደ ቤተክስቲያኑ ሲያመሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ያደረጉት ነጠላ ጫማ አንዱ እግርጭቃ ይዞ ያስቀርባቸዋል፡፡ ቅዱስ አባታችንም በጭቃ የተዋጠ ጫማቸውን ከማንሳት ይልቅ አንዱን አውልቀው በእግራቸው ቤተክርስቲያኑ ያለበት ቦታ ደርሰው መቃኞውን ባርከው ከደብረ ሰላም ቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከመጡት ካህናት ታቦቱን ተረክበው ቤተክርስቲያኑን ባርከው ታቦቱን አስገብተው ወደ መንበረ ፓርትርያርክ ተመለሱ፡፡
ለአካባቢው ምዕመን በተደረገው ጥሪ መሠረት ሐምሌ 29 ለሐምሌ 30 አጥቢያ ሌሊት ማሕሌት ተቁሞ ጠዋት ቅዳሴው ተቀድሶ ታቦቱ ወጥቶ በጅምር ላይበነበረው እስካሁን አገልግሎት ሲሰጥ በነበረው ሕንፃ ቤተክርስቲያን ታቦቱ ኡደት አድርጎ በዓሉ በሰላም ተጠናቋል፡፡
ይህ ከሆነ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር አድካሚና እልህ አስጨራሽ ውጣ ውረዶች በኃላ በአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ያላሰለሰ ጥረት ታክሎበት በቤተክርስቲያ ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ አባላት ብርታት ሕንፃ ቤተክርስቲያኑ ተጠናቆ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ መቃኞ ሆኖ ሲያገለግል የነበረውም ለቤተልሔም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ ተቀይሮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡
ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል መቼ ተመሰረተ?
የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል በአካባቢው የሚገኝ ህዝበ ክርስቲያን በአቅራቢያቸው ቤተክርስቲያን ባለመኖሩ በእለተ ሰንበትና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ በዓላት በቅርብ እየተገኙ ከፈጣሪያቸው ጋር በጸሎት የሚገናኙበት ስጋውን ደሙን የሚቀበሉበት ቤተ እግዚአብሔር እንዲሰራ ህዝበ ክርስቲያኑ ስላመነበት ይህን ቤተከርስቲያን ምእመናን በማስተባበርና አስተዋጽኦ (አርዳታ) በመሰብሰብ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ህዳር26 ቀን 1969 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡
በዚህ መሰረት ስራውን ጀምሮ የካቲት 6 ቀን 1969ዓ.ም በሶስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተከለ ሐይማኖት አማካኘነት የመሰረት ድንጋዩን በማኖር ቦታውን ባርከው የማበረታቻ ምክር ሰጥተው ጸሎተ ወንጌል እንደተፈጸመ በእለቱ በስፍራው ተገኘተው ህዝበ ክርስቲያን የልግስና እጁን መዘርጋት ቀጠለ፡፡
በዚህ መሰረት የተገኘውን አነስተኛ ገንዘብ በመያዝ ስራው ግንቦት 14 ቀን 1969 ዓ.ም ተጀምሮ ሐምሌ 28 ቀን 1969 የመጀመሪያው መቃኞ ስራ ተጠናቀቀ።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
+251961292926
ኢሜል
etsepatosst@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
07 • ጉለሌ • አዲስ አበባ
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ