Sunday SchoolActive

መንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል

Menbere Mengiset (Gebi) Gabriel Monastery

ዓምደ ሃይማኖት

ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ትውልድን በሃይማኖት በምግባር እያነፀ አስካሁን ዓሥርት ዓመታት ተጉዟል፡፡ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ለዲቁና፣ ለቅስና፣ ለመምህርነት፣ ለቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት የበቁ ካህናት፣ በሥጋዊ ትምህርት ደረጃቸውም አንቱ የተባሉ ለአገር ለወገን የሚበጁ አገር (ሕዝብ) የጣለባቸውን አደራ በአግባቡ የሚወጡ ታማኝ ዜጎች ተገኝተውበታል፡፡ በቅ

06 • አራዳ • አዲስ አበባ
1957 ዓ.ም
+251966710052
Menbere Mengiset (Gebi) Gabriel Monastery
Menbere Mengiset (Gebi) Gabriel Monastery

Sunday School

Menbere Mengiset (Gebi) Gabriel Monastery

06 • አራዳ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

መንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

ለሕፃናትና ለወጣቶች ወንጌልን በማዳረስ ለቤተክርስቲያን ተተኪዎችን ማፍራት፤

የእኛ ራእይ

ሕፃናትና ወጣቶች የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ዐውቀውና አክብረው በሃይማኖትና በምግባር ጸንተው ሲኖሩ ማየት፤

የእኛ እሴቶች

ፍቅረ እግዚአብሔር

ፍቅረ ቢጽ

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

መንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል

ዓምደ ሃይማኖት

ስለ አመሰራረቱ

የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት በፈቃደ እግዚአብሔር በብፁዕ አቡነ  እንድርያስ  አሳሳቢነት   የተወሰኑ  ዲያቆናት በጥቂት  የአጥቢያው  ወጣቶች   አማካኝነት  በ1957  ዓ.ም  "ዓምደ ሃይማኖት የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር"   በሚል ስያሜ ተመሰረተ ፤

ስለ እኛ

ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ትውልድን በሃይማኖት በምግባር እያነፀ አስካሁን ዓሥርት ዓመታት ተጉዟል፡፡ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ለዲቁና፣ ለቅስና፣ ለመምህርነት፣ ለቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት የበቁ ካህናት፣ በሥጋዊ ትምህርት ደረጃቸውም አንቱ የተባሉ ለአገር ለወገን የሚበጁ አገር (ሕዝብ) የጣለባቸውን አደራ በአግባቡ የሚወጡ ታማኝ ዜጎች ተገኝተውበታል፡፡ በቅዱስ ጋብቻ ጻንተው እየኖሩ ያሉ ምእመናን ፈርተውበታል፤ ሕፃናት  በሥነምግባር  እየተኮተኮቱ  አድገውበታል፤ ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት በ60 ዓመት ጉዞ በርካታ አገልግሎቶችን አከናውኗል እያከናወነም ይገኛል፡፡

መንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

ዳግማዊ ንጉሥ አጼ ምኒልክ ከአዲስ አበባ ከተማ መቆርቆር በኋላ በቤተ መንግሥታቸው አቅራቢያ ሥዕል ቤት ኪዳነ ምህረትን አሠርተው አመቤታችንን በጸሎት ይማጻኑ ነበር፡፡ የመልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ታቦትም ከአጠገባቸው አንዲኖር ተመኙ ፡፡ ከዚያም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን እንዲያመጡላቸው ለቅርብ ወዳጆቻቸው ነገሩ . ፣ባለሟሎቻቸው ከብዙ ፍለጋ በኋላ በቡልጋ አውራጃ ከሰም ወረዳ ‹ንግቤ አባ ቀውስጦስ » ከሚባል አካባቢ ከጥፋት መልዕከተኛው በግራኝ አሕመድ ወረራ ወቅት ከጥፋት በማሸሸ በዋሻ ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን የቅዱስ ገብርኤልን ጽላት አመጡላቸው ዳግማዊ ጉሥ አጹ ምኒልከም ቤተ መቅደሱን እስኪያሳንጹ ለጊዜው በስዕል ቤት ኪዳነ ምህረት እንዲቀመጥ አስደረጉ ፤

ታቦተ ቅዱስ ገበርኤል ለ6 ዓመት በስዕል ቤት ኪዳነ ምህረት ተቀመጠ፣፤ ያለ ቅዳሴ መቀመጥ እንደ ሴለበት ፀሐፌ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ እና ሊቀ ካህናት አለቃ አስጢፋኖስ ተመካከረው ለዳግማዊ እጹ ምኒልክ በቅዱስ ገብርኤል ስም ቤተከርስቲያን እንዲታነጽ ነገሯትችው ፡፡

በወቅቱም የጣሊያን ጦር አገርን በወረረ ጊዜ ንጉሥ አፄ ምኒልክ ድንበር ለማስከበር ፣ወራሪውን የጣሊያን ጦር ከአገር ለማስወጣት ፣ለነጻነት ሊዋጉ ወደ አድዋ ለመዝመት ዝግጅት ላይ ነበሩና ለቅዱስ ገበርኤል ስዕሰትን ተሳሉ ፡:አገሬን ከጠላት ከተቃጣባት ጥቃት ከፈጣሪህ አማልደህ ድል እናደርግ ዘንድ አርዳን 1ጠላትን ድል አድርጌ ስመለስ ቤተ መቅደስህን አንጻለሁ በማለት ብፅዓት ገቡ (ተሳሉ) ፡፥

ከአድዋ ጦርነት በኋላም ኢትዮጵያውያን በወራሪው የጣሊያን ጦር. ድል ተጎናጽፈው ፣ድንበር አስከብረው ፣ወራሪውን ጠላት አሳፍረው ሲመለሱ፤ ዳግማዊ ንጉሥ አፄ ምኒልከ በገቡት ብፅዓት (ስዕለት) መሠረት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በ1889 ዓ.ም አሳነጹ፡፥ ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ሲታነጽ ባለ ስምንት ማዕዘን ክብ ቅርጽ የሆነ  ሲሆን ሰላሳ ስምንት ቋሚ ምሰሶዎች አሉት በወቅቱ የሣር ከዳን የነበረ ሲሆን ቆይቶም ጣሪያው ቆርቆሮ እንዲለብስ ተደርጓል፡፡የውስጠኛው ጣሪያ ኮርኒስ ድንቅ ጥበብ ይንጸባረቅበታል፨ ስልጣኔ ያኔ በከተማዋ ዘልቆ ባልነበረበት በዚያ ዘመን እንዴት ሠሩት? በሚያስብል መልኩ ግርምትን ይፈጥራል፡፡ከቅኔ ማኅሌት ወደ ቅድስት መግቢያ በሮች ማዕዘን በአስደናቂ ሁኔታ ወጥ ከሆነ የጥድ እንጨት የተሠሩ ናቸው፡፡ በመቅደሱ ግድግዳዎች ዶግማን (ሃይማኖትን) የሚያስተምሩ ፣ከብረ ቅዱሳንን የሚገልጡ፤ ታሪከን የሚነግሩ ልዩ ልዩ እጅግ የተዋቡ ቅዱሳት ስዕላት የተዋበ ነው፡ aaaaa

የመንበረ መንግሥት(ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በ1989 ዓ.ም. በንጉስ አጼ ምኒልክ ተመሰረተ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251966710052

ኢሜል

amdehaymanot19@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

06 • አራዳ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

Menbere Mengiset (Gebi) Gabriel Monastery

Address

06 • አራዳ • አዲስ አበባ

Lat 9.02423Lng 38.76211
Open in Google Maps