Sunday SchoolActive

ለቡ ደብረታቦር በዓለወልድ እና አበ ብዙሃን አብርሃም ቤተክርስቲያን

Lebu Debre Tabor Bealewold and Abune Abrham Church

ኆኅተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

ሰንበት ትምህርት ቤታችን መዋቅራዊ አቅሟ ጎልብቶና ተደራሽነቷ ሰፍቶ ፣የመማር ማስተማር ሂደቷ  አባላት በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ተዋህደው የቤተ ክርስቲያን አልኝታና መከታ እንዲሆኑና የሀገር ፍቅር  እንዲኖራቸው ማድረግ

01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
1996 ዓ.ም
+251943172591
Lebu Debre Tabor Bealewold and Abune Abrham Church
Lebu Debre Tabor Bealewold and Abune Abrham Church

Sunday School

Lebu Debre Tabor Bealewold and Abune Abrham Church

01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

ለቡ ደብረታቦር በዓለወልድ እና አበ ብዙሃን አብርሃም ቤተክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ ለማፍራት የሰንበት ት/ቤታችን አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነው  ሥርዓት ትምህርት በማስተማርና የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ ዘመኑን በዋጀ አሠራር በመጓዝ ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ሰርቶ ማሳየት

የእኛ ራእይ

የቤተክርስቲያን ዶግማ ፤ስርዓት እና ትውፊት ጠብቆ በማስጠበቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ ነው፡፡

የሰንበት ት/ቤቱ አባላት በቤተክርስቲያን በዕውቀታቸው በገንዘባቸው በጊዜያቸው እንዲያገለግሉ ሁኔታቸውን ማመቻቸት፡፡

የእኛ እሴቶች

1.እግዚአብሔርን መፍራት

2.በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ማመን

3.በመላዕክትና በቅዱሳን አማላጅነት ማመን

4.ለሰው ሁሉ ክብር መስጠት

5.በተግባር የተገለጠና በፍቅር አገልግሎት መስጠት

6. ዘመኑን ማወጀት

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

ለቡ ደብረታቦር በዓለወልድ እና አበ ብዙሃን አብርሃም ቤተክርስቲያን

ኆኅተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

በ1995 ዓ.ም የደብራችንን መመስረት ምክንያት በማድረግ የደብሩ ካህናት የአካባቢውን ልጆች በመሰብሰብ አቋቋሙ ነገር ግን በተጠናከረ ሁኔታ ስላልተያዘ ተበተነ ዳግመኛም በ1996 ዓ.ም በአንዲት እህት አማካኝነት ዳግም የተበተኑት አባላት ተሰብስበው አገልግሎት የጀመሩ ሲሆን በዛኑ ዓመት በወቅቱ በነበሩት የደብሩ አስተዳዳሪ መምህር አሰበ በተባሉ አባት የመጀመሪያውን ሰብሳቢ በመምረጥ እንዲሁም ክፍላትን በማዋቀር በመዋቅር ደረጃ አገልግሎቷን አጠናክራ ለዛሬ ደርሳለች።ኆኅተ ሕይወት ማለት የሕይወት ደጅ ማለት ነው፡፡

ስለ እኛ

ሰንበት ትምህርት ቤታችን መዋቅራዊ አቅሟ ጎልብቶና ተደራሽነቷ ሰፍቶ ፣የመማር ማስተማር ሂደቷ  አባላት በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ተዋህደው የቤተ ክርስቲያን አልኝታና መከታ እንዲሆኑና የሀገር ፍቅር  እንዲኖራቸው ማድረግ

ለቡ ደብረታቦር በዓለወልድ እና አበ ብዙሃን አብርሃም ቤተክርስቲያን

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቱን ትውልድ በአምልኮተ እግዚአብሔርን አፅንቶ በሃይማኖትና በምግባር ከማኖርም ባሻገር ለቤተ ክርስቲያን ቀናኢ የሆኑ አገልጋዮችን አፍርቷል፤ በማፍራት ላይም ይገኛል። ሰንበት ትምህርት ቤት በዕለተ ሰንበትና አበይት በዓላት ወቅት ያሬዳዊ መዝሙራትን ከማቅረብም በላይ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትን፣ ቆሞሳትን፣ ጳጳሳትን፣ መምህራነ ወንጌልን፣ ሰባኪያንን እና በልዩ ልዩ አገልግሎት ላይ የሚፋጠኑ ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችን ለቤተ ክርስቲያናችን አበርክቷል። ይህ አገልግሎት እንዳይቋረጥና ቤተ ክርስቲያን ለትውልድ ሁሉ ከነሙሉ ክብሯ ትተላለፍ ዘንድ በያለንበት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤትን ማጠናከር የዘወትር ተግባር ሊሆን ይገባል።

የለቡ ደብረ ታቦር በዓለወልድ እና አበ ብዙኃን አብርሃም ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው በሚገኙ የመሬት ባለቤቶች በተሰጠ ቦታ ላይ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በሆነ መቃኞ ተሰርቶ ታቦተ እግዚአብሔር ወልድን በማስገባት ጥር 20 ቀን 1995 ዓ.ም የተቋቋመ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ታቦተ እግዚአብሔር ወልድ በቦታው እንዲመጣ ምክንያት የሆነው በአካባቢው ከ1937 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመ የበዓለወልድ እድር ነው።

በቆርቆሮ የተሰራው መቃኞ ለ4 ዓመታት ካገለገለ በኋላ ስመ ክርስትናቸው ብርሃነ ገብርኤል የተባሉ ባለሀብት ምዕመን ደረጃውን የጠበቀ ቤተክርስቲያን ለመስራት በመወሰንና ይኽንኑ ለሚመለከታቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበላይ ሐላፊዎች በማሳወቅ ተፈቅዶላቸው አሁን ያለውን ህንጻ ቤተክርስቲያን አንጸዋል።

የግንባታ ሥራው ተጀምሮ ከተጠናቀቀ በኋላ በወቅቱ በነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ  በብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ  ጳውሎስ ነሐሴ 28 ቀን 1999 ዓ.ም ተባርኮ ጽላቱ በአማረ ሁኔታ ደረጃውን ጠብቆ ወደተሰራው አዲስ  ህንፃ እንዲገባ ተደረገ፡፡

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251943172591

ኢሜል

hohitehiwot@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

Lebu Debre Tabor Bealewold and Abune Abrham Church

Address

01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

Lat 8.94378Lng 38.58585
Open in Google Maps