የጃቴ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን
Jate Saint Kidane Mheret Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
የሰ/ት/ቤቱ ዐበይት ተግባራት ፩. የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሃይማኖት እና ሥርዓት ጠብቆ፣ሳይለወጥ(ሳይቀላቀል)፣ሳይበረዝ በቀጥታ ለትውልድ ማስተላለፍ ፡፡ ፪. ማንኛውም ምዕመን ሃይማኖቱን እና የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል አንዲያውቅ እና እንዲረዳ ማድረግ ፡፡ ፫. የተለያዩ መናፍቃን ልዩ ልዩ ዘዴ በመጠቀም በቅድስት ቤ/ክ ውስጥም ሆነ ውጭ ሾልከው በመግባት የቤ/ክ ልጆች …

Sunday School
Jate Saint Kidane Mheret Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
08 • አቃቂ ቃሊቲ (Akaki Kality) • አዲስ አበባ(Addis Ababa)
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
የጃቴ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ፡፡ ›› ማቴ ፳፰፥፲፱ ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ወንጌልን አመቺ በሆነ መንገድ ሁሉ ለመላው ዓለም መስበክ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ፣ሥርዓትና ትውፊት ተጠብቆ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ማፍራት ፡፡

፩ አገልጋይነት
የሰ/ት/ቤቱ አገልገሎት ሰማያዊ ዋጋ የሚያስገኝ መሆኑን በማመን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ልዩ ትኩረትና ክብር ይሰጣል፡፡
፪ ቅንነት
ሀ. ሰ/ት/ቤቱ ቅን አስተሳሰብ ለተሟላ አገልግሎት አሰጣጥ መሠረት መሆኑን ያምናል፣
ለ. በውይይትና በመግባባት የመሥራት ባህል ያምናል፣

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
የጃቴ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን
ፍኖተ ሰማዕታት ሰንበት ትምህርት ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
የሰ/ት/ቤቱ ዐበይት ተግባራት
፩. የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሃይማኖት እና ሥርዓት ጠብቆ፣ሳይለወጥ(ሳይቀላቀል)፣ሳይበረዝ በቀጥታ ለትውልድ ማስተላለፍ ፡፡
፪. ማንኛውም ምዕመን ሃይማኖቱን እና የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል አንዲያውቅ እና እንዲረዳ ማድረግ ፡፡
፫. የተለያዩ መናፍቃን ልዩ ልዩ ዘዴ በመጠቀም በቅድስት ቤ/ክ ውስጥም ሆነ ውጭ ሾልከው በመግባት የቤ/ክ ልጆች በዓርባ(፵) እና በሰማንያ(፹) ቀናቸው ያገኙትን የመንፈስ ቅዱስ ልጅነት በማሳደፍ እና በማጉደል የራሳቸውን ዓላማ እያቀራረቡ እና እየተመሳሰሉ ከሚመጡ ተኩላዎች እንዲጠበቁ ማድረግ እና ልዩ ልዩ ዓይነት እንቅስቃሴያቸውን በመግታት የቀደመ እምነታቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ ፡፡

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የጃቴ መካነ ህይወት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ቅናት ባደረባቸው ጥቂት የአጥቢያ ወጣቶች በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን ለመማር እና ብሎም ቤተ ክርስትያንን ለማገልገል ካላቸው መንፈሳዊ ሀሳብ የተነሳ በ1973 ዓም ተመሰረተ። በወቅቱ በነበረው ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እና የቤተሰብ የተሳሳተ ግንዛቤ የወጣቶችን መስባሰብ በሌላ መንፈስ በመመልከት ወደ ቤተ ክርስትያን አንዳይሔዱ ተፅዕኖ ቢደረግባቸው ያን ሁሉ ችግር በፅናት ተጋፍጠው ዛሬ ላይ እንዲህ አብቦና አፍርቶ የሚታየውን ሰንበት ት/ቤታችንን ለመመስረት ይህ ነው ብለን ልንገልጸው የማንችለው መሰዋዕትን በመክፈል በዕለተ ሰንበት ብቻ በመሰባሰብ መዝሙር በማጥናት እና አልፎ አልፎ መምህራን ሲያገኙ ቃለ እግዚአብሔርን በመማር ብቻ በቤተ ክርስትያን ታዛ ስር በመሰባሰብ እንደጀመሩ የሚናገሩ ዛሬ ላይ በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርተው የሚገኙ የሰንበት ት/ቤታችን መስራች እህት ወንድሞቻችን ያጫውቱን ታሪክ ነው :: ታዲያ በዚህ መንፈስ የተመሰረተችው ሰንበት ትቤታችን ከግዜ ወደ ግዜ ለመቅረፍ አባላቱን ይዘው ከቤተ ክርስትያናችን አባቶች ጋር እያደገች በመምጣት የሕፃ ናትና የወጣቶችን ጉባኤ በማመቻቸት በሳምንት ለ2 ቀን ቅዳሜና እሑድን በመጠቀም ከታዛ ስር በመነ ሳት በቤተ ክርስትያናችን ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የክርስትና ቤት እና ደጀ ሰላምን ከአባቶች ጋር በ መመካከር በማስፈቀድ ሲገለገሉበት ቢቆዩም ከዕለት ወደ ዕለት የአገልግሎት እና የአባላቶች መጨመር በወቅቱ በነበሩ የሰ/ት/ቤታችን የሥራ አመራር አባላት የቦታ ችግር እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ ቢሆንባቸ ውም ያንን ችግር በመመካከር ለትውል ድ የሚተላለፍ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ አዳራሽ ለመስራት ቦታ ከተረከቡ በኃላ በ1983ዓ.ም ግንባታ ው በይፋ ለመጀመር በቅተዋል።
ሰንበት ትምህርት ቤታችን በወቅቱ ከምትሰጠው አገልግሎት አንፃር እና ሁናቴ በመነሳት ይኽን አዳራሽ ሰርቶ ለመጨረስ የነበረውን ስሜት ዛሬ ላይ ሆነን ስናስታውሰው በአንድ ቀን ተሰርቶ ለመጨረስ የታለመ ይመስል ነበር፡፡ በግንባታው ወቅትም የነበረ የአባላቱ ተሳትፎም ወንድም እህቶቻችን ቀን በትምህርት እና በስራ ገበታ ቸው ላይ ውለው ማታ ላይ በቤተክርስትያናችን አዳር በመሰባሰብ በወቅቱ ለግንባታ የተመረጠው ቦታ እለት የበዛበትና እና ያልተስተካከለ ቦታ ከመሆኑ አንፃር ለሊቱን በጎማ ድንጋዩን ሲያቃጥሉ አድረው ሲነጋ ወደ ስራ እና ትምህርታቸው ሲጓዙ ሌሎች ደግሞ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የሚመቻቸው አባላት ያን ድንጋይ በመፍለጥ እና ቦታውን በመቆፈር በማስተካከል ይህ ነው ተብሎ ዛሬ ላይ ለመናገር በሚያ ዳግት መስዋትነት የአዳራሽ የግንባታ ቦታውን በመደልደል የሰሩትን ስራ ዛሬ በቅርስነት የያዝነው የፎቶ ማስታወሻችን ያወራል። በዚህ መልክ የተጀመረው የሥብከተ ወንጌል አዳራሽ ግንባታ ስራ የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥመው እና አላማቸው እንዳይታጎል የትምህርት ፕሮግራማቸው በማስተካከል ቀኑን ሙሉ በሐገራችን ትልቁ መጋቢ መንገድ (የጅቡቲ መስመር) በመውጣት በፈረቃ በሙዳይ ምዕዋት ስራ በሚገኝ ገቢ በእግዚአብሔር አምላክ አጋዥነት ግንባታችን እየተፋጠነ ጥቂት ዓመታትን ብዙ ውጣ ውረድ የበዛበትን የግንባታ እና የአገልግሎት ግዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ አዳራሻችንን ለማስመረቅ በሚጓጉበት ወቅት በሁለት ዓመት 2 ግዜ በደረሰብን የመኪና አደጋ ክተገጨብን 9 ልጆች መካከል 1 እህት 2 ወንድሞች ወዲያው በሞት ስናጣ ቀሪዎቹ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ::
የመጀመሪያ አደጋ በ1987 ዓ.ም 3 ልጆች ሲገጨብን አንድ እህታችን በልጅነት ዕድሜዋ በሞት ተለይታናለች። በወቅቱ የደረሰብን አደጋ ድንጋጤ ቢፈጥርብንም ከሃዘናችን በመረጋጋት የተረበሹ ቤተሰቦቻችን በማስረዳት ለተወሰኑ ቀናት ተቋርጦ የነበረውን የሙዳይ ምዕዋት ስራችንን እንደ ቀድሞ በትጋት እየሰራን አዳራሻችንን መስከረም ለማስመረቅ በወርሃ ነሐሴ 1988 ዓ.ም ከበፊቱ እጅግ በከፋ መልኩ 6 ልጆቻችን ሲገድልብን 2 ወንድሞች በሞት ሲለዩን 4 ለአካል ጉዳት በመዳረጋቸው ትልቅ ሀዘን ውሥጥ ሳለን ቤተሰቦቻችን ሆ ብለው በመነሳት ቤ/ክ አንዳንሔድ ብንከለከልም እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሚለውን አምላካዊ ቃል በመያዝ ከቤተሰቦቻችን ጋር በመሰብሰብ በመወያየት ሃሳባችንን በማስረዳት አዳራሻችንን ለማስመረቅ ሌት ከቀን ደፋ ቀና በማለት አስፈላጊ ነገሮችን በማሟላት መጠኑ 9ሜትር በ24 ሜትር የሆነ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከ4 ቢሮዎች እና ከሙሉ ወንበሮች ጋር መስከረም 12 ቀን 1989ዓ.ም ብዕዑ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ በተገኙበት ለማስመረቅ በቅተናል :: በዚህ መሰረት የተቀጣጠለው የሰት/ቤታችን የረጅም ጉዞ አንድ እርምጃ እየጨመረ በመምጣት በወቅቱ አዳራሻችን ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ከሚስጠው አስተዋፅኦ ባሻገር ለመንፈሳዊ ሰርግ እና ለስብሰባዎች አገልግሎት እየሰጠ አስከ 1994 ዓ.ም መስከረም ወር ድረስ ከቆየ በኃላ ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ እና የሰንበት ት/ቤቱ ስራ አመራር አባላት ጋር በቀጣይ ሊሰራ ለታሰበው አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ወቅት መቃኛ ከመስራት ባማረው አዳራሻችን የእመቤታችን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲገባ በአንድ ድምፅ ስንስማማ እኛም ወደ ቀደመ ታሪካችን ወደ ዛፍ ጥላ እና ላስቲክ አዳራሻችን በመግባት አገልግሎታችንን በማፋጠን ቀድሞ በ2 ክፍል ብቻ ይሰጥ የነበረው የሰንበት ትቤታችን ትምህርት ዛሬ ላይ ወደ አስር ክፍል በማሳደግ ለዚህ የምርቃት በዓላችን በመብቃታችን አምላካችንን እጅግ አድርገን እናመስግናለን።
እንግዲህ የአራት አስርት አመታት ባለቤት የሆነችው ሰንበት ት/ቤታችን በአዲሱ ህገ ቤተ ክርስትያናችን ግንባታ ላይ ያሳደገቻቸው ልጆቿ በኮሚቴነት በመወከል የራስዋን አስተዋፅኦ ብታደርግም ከላይ እንደገለፅነው ከመማር ማስተማር ውጪ ያገለግለን የነበረውን ትልቅ የገቢ ምንጫችንን አዳራሻችን 7 ለመቃኞነት ከመስጠት አንስቶ በጉልበት በዕውቀትና እንዲሁም በገንዘብ ከ50,000 ሺ ብር በላይ በተለያዩ ጊዜያት ለአዲሱ ህንፃ ቤ/ክ በመለገስ በመማር ማስተማር ሒደትም ህፃናትን እና ወጣቱን ለ የብቻ በዕድሜ እና በትምህርት ደረጃቸው በመከፋፈል ብዛታቸው ከ600 በላይ አባሎችን በማስተማር ላይ እንገኛለን በተጨማሪም በክፍለ ከተማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለበሲቃ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና ለደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ተማሪዎች እና መምህራን የግቢ ጉባኤ ትምህርት በመጀመር ዛሬ ላይ ከ400 በላይ አባሎች ስናስተምር ለትምህርቱ መሳካት መጠነኛ ቤተ መፀሐፍት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን ። በልማትና በጉ አድራጎት ስራም በአመት አንድ ጊዜ የትንሣኤን ዕለት ቁጥራቸው ከ500 በላይ ነደያን የትንሳኤ በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ የምሳ ግብዣ ስናደርግ በቤተ ክርስቲያናችን ዙርያ ለሚያድሩ ቁጥራቸው16 ለሚደርሱ ነድያን ግዜያዊ መጠለያ የሽራ ላስቲክ አንሶላ ፍራሽ በየአመቱ እየረዳን ስንገኝ በአመት ሁለት ጊዜ ለዘመን መለወጫ እና ለትንሳኤ በዓል እንዲሁ የህግ ታራሚዎችን በአዲስ አበባ የ ሕ ግ ታራሚዎች ማቆያ ቃሊቲ በመሔድ እስረኞችን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እየሰጠንና እየጎበኘን እንገኛለን በተያያዘ መልኩ ለአካባቢ ምዕመን መጠነኛ አገልግሎት የምትሰጥ የመዝሙር እ ና የመጸሐፍት መሸጫ ሱቅም አገልግሎት በመስጠት ስንገኝ በተጨማሪም በሰንበት ት/ቤታችን ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን በዓመት 4 ግዜ በተለያየ ግዜ አጭር እና ረጅም ጉዞዎች ለአባላቶች በማዘጋጀት ሃይማኖታዊ ቦታዎችን እንዲያውቁ እና በቅዱሳን ገድላት አድባራት በረከት እንዲያገኙ በማድረግ በመስራት ላይ እንገኛለን ፡፡
በመጨረሻም ማንኛውም የአካባቢው ወጣቶችም ሆናችሁ ወላጆች ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት ተመልክታችሁ ሁላችንም እውቀት ያለው በእውቀቱ ጉልበት ያለው በጉልበቱ እና ገንዘብ ያለው በገንዘብ ቤክ ድናገለግል መልዕክታችንን እያስተላለፍን ከ1994ዓ.ም ጀምሮ በሞት በተለዩን ወንድም እህቶቻችንን መታሰቢያነት ፍኖተ ሰማዕታት የሰንበት ት/ ቤቱ መጠሪያ ሆነ ። የጃቴ መ/ሕ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የፍ/ሰማዕታት ሰ/ት/ቤት ‹‹አገልግሎታችንን እግዚአብሔር ይባርክልን››
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
+251940398758
ኢሜል
jatefenotesemaetat@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
08 • አቃቂ ቃሊቲ (Akaki Kality) • አዲስ አበባ(Addis Ababa)
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ