አቃቂ ፋንታ ደብረ ፅጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን
Akaki Kality St.Rufael & St.Arsema Church
ሰንበት ትምህርት ቤቷ ለአካባቢው ምእመናን፣ወጣቶች፣ጎልማሶች፣ለህፃናት በተከታታይ እና በርእቀት መንፈሳዊ ተከታታይ ትምህርቶችን፣ የአብነት ትምህርት፣ያሬዳዊ ዝማሬ ስልቶችን እና የቤተክርስቲያኗ የዜማ መዛሪያ ከሆኑት የበገና ትምህርቶችን ገፅለገፅ እና እንዲሁም ዘመኑን በዋጀ መልኩ በማህበራዊ ሚዲያ እያስተማረች የድርሻዋን እየተወጣች ትገኛለች።

Sunday School
Akaki Kality St.Rufael & St.Arsema Church
1 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
አቃቂ ፋንታ ደብረ ፅጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

1. ‹‹ሒዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችሁ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው››፡፡ማቴ ፳፰፥፲፱ ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ወንጌልን አመቺ በሆነ መንገድ ሁሉ ለመላው ዓለም መስበክ፡፡

1. የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና ስነ- ስርዓት ተጠብቆ ሣይለወጥ ሳይበረዝ በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ፡፡

2. ህፃናትና ወጣቶች በእምነት እና በክርስቲያናዊ ስነ ምግባር እንዲያድጉ ማድረግ ፡፡

ፍቅር

ትህትና

ታዛዥነት

በጎነት

ትዕግስት

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
አቃቂ ፋንታ ደብረ ፅጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን
ፍኖተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
ሰንበት ትምህርት ቤቷ ለአካባቢው ምእመናን፣ወጣቶች፣ጎልማሶች፣ለህፃናት በተከታታይ እና በርእቀት መንፈሳዊ ተከታታይ ትምህርቶችን፣ የአብነት ትምህርት፣ያሬዳዊ ዝማሬ ስልቶችን እና የቤተክርስቲያኗ የዜማ መዛሪያ ከሆኑት የበገና ትምህርቶችን ገፅለገፅ እና እንዲሁም ዘመኑን በዋጀ መልኩ በማህበራዊ ሚዲያ እያስተማረች የድርሻዋን እየተወጣች ትገኛለች።

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
- በቤተ ክርስቲያኗ ቤተ መቅደስ ዉስጥ ካለው የንብ መንጋ በአመት 2 ጊዜ ለምዕመናን የማር ጸበል ይሰጣል ፡፡
- ቤተ ክርስቲያኗ ለምዕመናን የሚያገለግል የተፈጥሮ 22 ጸበል ያላት ሲሆን ከሩቅ መተው ለሚጸበሉ ምዕመናን ማረፊያ አዳራሽ ሰርታ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች ፡፡
ቀደም ሲል 1930ዎቹ ገደማ አባ ፈንታ እየተባሉ የሚታቁ የበቁ አባት በወንዞቹ አካባቢ በመሆን ፀሎት ያደርጉ ነበር ፡፡የወንዙም ስያሜ በእሳቸው ስም ፋንታ እየተባለ መጠራት እንደጀመረ አንዳንድ አባቶች ይናገራሉ፡፡ አባ ፈንታ ፀሎት በሚያደርጉበት ቦታ ብዛት ያለው ፀበል በስፍራው ፈልቆ ነበር ፡፡ከእሳቸውም በኃላ አባ ተካ ሚባሉ አባት ይህንን ፀበል እያጠመቁ ለዘመናት ከቆዩ በኃላ ምክንያቱ በማይታወቅ ነገር ይህ ፀበል ደረቀ ፡፡ እርሳቸውም ማጥመቁን አቆሙ፡፡
ይህ በእንዲ እያለ ነበር በ1999 በወርሃ ሀምሌ አቶ ሀይሉ ክብረት የተባሉ ግለሰብ ይህ ቦታ እኮ እኛ ልጆች ሆነን ፀበል እንጠመቅ ነበር ከጊዜ በኃላ ግን ፀበሉ በመድረቁ ምእመናን ተበተኑ አሁን ደግሞ ፀበሉ ፈልቆ በአካባቢው የሰፈሩት ሰዎች ፀበሉን እየቀዱ ለመጠጥነት ብሎም ለግል ንፅ ህና እያዋሉት ስለሆነ ከ ዚህ አካባቢ ቤተክርስቲያን እንዲሰራ የአ ካባቢውን ምእመናንን በመቀስቀስ 497 የሚያህል የህዝብ ፊርማ አሰባስቦ በ1999 በሀምሌ ወር መቋኞ ቤት አሰሩ፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ የቀበሌ 01/03 በአዲሱ አጠራር ወረዳ 1 አስተዳደር ጽ/ቤት ህገ ወጥ ቤት ሰራችሁ በማለት መቋኞ ቤቷን ካፈረሱ በኃላ ከብዙ ውጣውረድ በኃላ ልክ በፈረሰ በአመቱ የቁስቃም ማሪያም አገልጋይ የነበሩት መላከ ምህረት ቀሲስ ዳዊት ስብሃት አንድ የበቁ አባት መቋኞ ቤቷን መፍረሷን ከነገሯቸው በኃላ ሄደው ይህንን ቤተክርስቲያን እንዲያቋቁሙ ገልፀውላቸው ወደ እዚህ ስፍራ ላኳቸው፡፡ እኚህ አባት ከብዙ ውጣውረድ በኃላ በፈረሰቸው መቋኞ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢው ይኖሩ ከነበሩት ከአቶ ተሾመ ወልዴ ጋር በመገናኘት የመጡበትን ሁሉ ገልፀውላቸው የፈረሰውን መቋኞ ቤተ-ክርስቲያን እንዲያሰሩዋቸውና ስለ ፈረሰችው መቋኞ ቤተ-ክርስቲያን ያለፈ ታሪኩን እንዲነግራቸው ጠይቀው ሁሉንም ነገር ከነገሩዋቸው እና ስፍራውን ካሳዩዋቸው በኃላ ለ26/11/2000 ዓ.ም ቀጠሮ ተያይዘው ተለያዩ፡፡
አቶ ተሾመ ወልዴም በተባሉት ቀን የአካባቢውን ነዋሪ ሰብስበው ተገናኙ እና በዕለቱ መስራች ኮሚቴ መርጠው መቋኞ ቤተክርስቲያን መስራት ጀመሩ፡፡ ለስራቸውም ስኬት ሲሉ በወቅቱ የነበሩት አባቶች በ27/11/2000 ዓ.ም በጅምር መቋኞ ቤት ውስጥ ፀሎተ ምዕላ ተደረሰ፡፡በማግስቱም በ28/11/2000 ዓ.ም መቋኞ ቤተ-ክርስቲያና ተሰርቶ ተጠናቆ በ29/11/2000 ዓ.ም መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ፅላት ገብቶ ስርዓተ ቅዳሴ ተፈፀመ፡፡
መላከ ምህረት ቀሲስ ዳዊት ስብሐት ከመስራች ኮሚቴው ጋር በጋራ በመሆን ሁለተኛ ፅላት ህዳር 6/03/2001 ዓ.ም የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ፅላት እንዲገባ አድርገዋል፡፡ የቅድስት አርሴማ ፅላት በገባ በሳምንቱ የንብ መንጋ መጥቶ በመቋኞ ቤተ-ክርስቲያን ጉልላት ላይ አረፈ፡፡ በወቅቱ የነበሩት ካህናት የንብ መንጋውን ለመያዝ ሲሞክሩ ተነስቶ ሄደ፡፡ የንብ መንጋው በሄደ በሶስተኛው ቀን በራሱ ፍቃድ በድጋሜ በመምጣት ወደ ቤተ- መቅደስ በመግባት በታቦቱ በሶስተኛው መንበር ውስጥ ገባ፡፡ እስከዛሬ ድረስ ከማሩ እየተቆረጠ ከፀበል ጋር ለምእመናን እየተሰጠ ፈውስ እየሰጠ ይገኛል፡፡
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
+251981954946
ኢሜል
www.finotetsidiki13@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
1 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ