ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤተ-ክርስቲያን
Misrake Tsehay St. Gebriel, St. Arsema, and Father Adam Church
ሰንበት ትምህርት ቤታችን እንግዲ ከአመሠራረቷ እስከ አሁን ድረስ ከህፃን እስከ አዋቂ ድረስ በተለያየ የክፍል ደረጃ ከፋፍሎ በማስተማር ከሁለት ሺ (፳፻) እና አዚህ በላይ የሚሆኑ አባሎችን አብቅታለች።

Sunday School
Misrake Tsehay St. Gebriel, St. Arsema, and Father Adam Church
01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤተ-ክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ሳይለወጥ፣ ሳይበረዝ በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት።

ማንኛውም የቤተ-ክርስቲያን ተከታይ በተለይም ወጣቱ ትውልድ የሃይማኖቱን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት፣ ታሪክ፣ ባህልና ጥበብ እንዲያውቅ ማድረግ።

የሰ/ት/ቤቱ ዋና አላማ ጠንካራ አደረጃጀት ያለውና የበቁ አገልጋዮች ያሉባት መንፈሳዊ ተቋም ሆኖ ማየት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዐት እና ትውፊት ተጠብቆ ለምዕመናኑ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግና የተምሮ ማስተማር ሂደቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ።

የሰ/ት/ቤቱ አባላት ያላቸውን ሙያ፣ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት በማስተባበር ለቤተ-ክርስያን አገልግሎት እንዲያበረክቱ ማድረግ።

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤተ-ክርስቲያን
ፈለገ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
ሰንበት ትምህርት ቤታችን እንግዲ ከአመሠራረቷ እስከ አሁን ድረስ ከህፃን እስከ አዋቂ ድረስ በተለያየ የክፍል ደረጃ ከፋፍሎ በማስተማር ከሁለት ሺ (፳፻) እና አዚህ በላይ የሚሆኑ አባሎችን አብቅታለች።

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
በ ወርሀ ጥቅምት በ 1986 ዓ.ም ታቦተ ህጉ በእነ አቶ አፅብሀ በኩል ወደዚ ስፍራ መጣ እናም ፅላቱ በ ዘበኛ ቤት ውስጥ ያድር ነበር። የፅላቱ አመጣጥ በ ቅዱስ አባታችን በአቡነ ጳውሎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጲያ መልካም ፍቃድ ኤርትራ ስትገነጠል ከአሰብ ወደ ኢትዮጵያ ፈልሷል። ብፁዕ አባታችንም ዳግማዊ ቁልቢ ብለው ቦታውን ሰየሙ። በመቀጠልም የድንጋይ ህንፃ ብቻ ሳይሆን የሰው ህንፃም ሊታነፅ ይገባል በማለት ምስረታው ተጀመረ።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
+251953431142
ኢሜል
felegetsidksenbettmrtbet@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ