Sunday SchoolActive

ጀሞ ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን

Felege jordan saint john the baptist, holy virgin mary church

ፍኖተ ሠላም ሰንበት ት/ቤት

ሰ/ት/ቤት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው  እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት የትምህርት ቦታ ነች፡፡ ቤተክርስቲያናችን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት ስታካሒድ ኖራለች፤ ሰ/ት/ቤታችንም ከተመሰረ

ጀሞ 01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
1996 ዓ.ም
+251938040506
Felege jordan saint john the baptist, holy virgin mary church
Felege jordan saint john the baptist, holy virgin mary church

Sunday School

Felege jordan saint john the baptist, holy virgin mary church

ጀሞ 01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

ጀሞ ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

<p>የሰንበት ትምህርት ቤቱ ተልእኮ በማቴ 28፥19 “እንግዲህ ሂዱና በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፡፡” የሚለውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ትምህርተ ወንጌልን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለሕፃናት፣ ለወጣቶች እንዲሁም ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ተተኪዎችን ማፍራት ነው፡፡&nbsp;</p>

የእኛ ራእይ

<p>‹‹ህፃናት ወደኔ ይመጡ ዘንድ ተዋቸዉ አትከልክሏቸው›› ማቴ 19፤14 ‹‹የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› መክ 12፤1 ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ በተፃፈዉ መሠረት ህፃናትና ወጣቶች ሁሉ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት በጥበብና በሞገስ እንዲያድጉ ማድረግ፡፡</p>

የእኛ እሴቶች

<p>እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሰውን ማክበር፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ፣ ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣ ዘመኑን መቅደም መዋጀት</p>

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

ጀሞ ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን

ፍኖተ ሠላም ሰንበት ት/ቤት

ስለ አመሰራረቱ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት በአብነት ትምህርት ቤቶች ተማሪ ቁጥር እንዲቀንስ አደረገ። ሚሲዮናውያን ወጣቶችን ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው ለማራቅ ሲንቀሳቀሱ፣ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ደግሞ የራስ ማንነትን የመጠበቅ ስሜት ፈጠረ። በዚህ ምክንያት በ1936 ዓ.ም. በፈቃደኛ ወጣቶችና ካህናት አነሳሽነት የቅዳሜና እሑድ ትምህርት ቤቶች ተቋቋሙ። በ1970 ዓ.ም. ሰንበት ትምህርት ቤቶች በቃለ ዐዋዲ እውቅና ተሰጣቸው። ከ1983 ዓ.ም በኋላ የመንግሥት ተጽዕኖ ሲቀንስና የወጣቶች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ሲጨምር፣ በ1986 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ ወጣ።&nbsp; ይህንንም ደንብ መሰረት በማድረግ ሰ/ት/ቤታችን በ 1996 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡

ስለ እኛ

ሰ/ት/ቤት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው  እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት የትምህርት ቦታ ነች፡፡ ቤተክርስቲያናችን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት ስታካሒድ ኖራለች፤ ሰ/ት/ቤታችንም ከተመሰረተችበት 1996 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ዘርፍ ወጣቱን ከሕፃንነቱ ጀምሮ በማስተማር ለሰው ልጅ በሚያፈልጉት የአአምሮና የመንፈስ እድገት የተሟላ እንዲሆኑ ስትሠራ በተጨማሪም ማህበራዊ ግዴታዎቿን በመወጣት ላይ ትገኛለች

ጀሞ ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251938040506

ኢሜል

fnoteselamsundayschool@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

ጀሞ 01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

Felege jordan saint john the baptist, holy virgin mary church

Address

ጀሞ 01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

Lat 8.96369Lng 38.70650
Open in Google Maps