ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት
Mahidere Sibihat Holly Nativity to Mary and Debre Medhanit Medhanealem Churches
የሰንበት ት/ቤቱ አቋም በሃይማኖት ኑፋቄ፣ በሥርዓተ ቤተክርስቲያንና በሕገ ቤተክርስቲያን ጥሰት ካልሆነ በቀር በማንኛውም የቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ነገር ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሰ/ት/ቤቱን የሚጎዳ ሆኖ ሲያገኘው ድምፁን ያሰማል፡፡ በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ከሌሉ ወይም ደግሞ የቤተክርስቲያን እውቅና ከሌላቸው አካላት ጋር መንፈሳዊ አገልግሎትን…

Sunday School
Mahidere Sibihat Holly Nativity to Mary and Debre Medhanit Medhanealem Churches
ልደታ • አዲስ አበባ
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የአንዲቷን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የወንጌል ትምህርት በልዩ ልዩ የኅትመት ውጤቶችና ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለእምነቱ ተከታዮች ሁሉ በተለይም ለሕጻናትና ለወጣቶች ማድረስ፡፡ በእምነታቸው የጸኑ፣ የመናፍቃንን እንቅስቃሴ የሚገቱ፣ በተሰጣቸው ልዩ ልዩ ጸጋ ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ፣ ምሥጢራተ ቤተክርስያንን የሚካፈሉ በርካታ አባላትን ማፍራት፡፡

ዓላማ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት የሚጠብቁና የሚያስጠብቁ፤ ለቤተክርስቲያን በሚያስፈልጋትን ሁሉ ድጋፍ የሚሰጡ፤ በሥነ ምግባር የታነጹ፤ ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ ዜጎችን ማፍራት እና የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓተ ትምህርት ማስፋፋት፡፡

እሴት
አገልጋይነት
ታዛዥነት
ተቆርቋሪነት
አርአያነት

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት
የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
የሰንበት ት/ቤቱ አቋም
በሃይማኖት ኑፋቄ፣ በሥርዓተ ቤተክርስቲያንና በሕገ ቤተክርስቲያን ጥሰት ካልሆነ በቀር በማንኛውም የቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ነገር ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሰ/ት/ቤቱን የሚጎዳ ሆኖ ሲያገኘው ድምፁን ያሰማል፡፡
በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ከሌሉ ወይም ደግሞ የቤተክርስቲያን እውቅና ከሌላቸው አካላት ጋር መንፈሳዊ አገልግሎትን በማይጎዳ መልኩ በትብብር ይሠራል፡፡
በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ አይሳተፍም፡፡
በማንኛውም የፖለቲካ ተቋም ውስጥ በአባልነት የሚሳተፍ በሥራ አመራር ጉባኤና በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ በአባልነት መመረጥ አይችልም፡፡

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
አጥቢያ ቤተክርስቲያኗ ሁለት ቤተመቅደሶችን የያዘች ደብር ስትሆን በመታነጽ የምትቀምደው ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተመቅደስ ናት ፡ ሁለተኛው ቤተመቅደስ ደግሞ የደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተመቅደስ ነው።
በደብሯም ታቦታተ ህጉን በማውጣት በንግሥ በዓልነት የሚከበሩ በዓላት እንደሚከተለው ቀርበዋል
1ኛ) መስከረም 1 ቀን ዘመን መለወጫ (አዲስ ዓመት)
2ኛ) ጥቅምት 27 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት ዓመታዊ ክብረ በዓል (ጥቅምት መድኃኔዓለም)
3ኛ) ኅዳር 12 ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል (ኅዳር ሚካኤል)
4ኛ) ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል (ጽዮን ማርያም)
5ኛ) ጥር 12 ቀን በዓለ ቃና ዘገሊላ (የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያው ተአምር መታሰቢያ ክብረ በዓል)
6ኛ) ጥር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል መታሰቢያ (አስተርእዮ ማርያም)
7ኛ) መጋቢት 27 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለት ዓመታዊ ክብረ በዓል (መጋቢት መድኃኔዓለም)
8ኛ) ግንቦት 1 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል መታሰቢያ (ልደታ ለማርያም)
9ኛ) የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት (የቀመር በዓል --- ከበዓለ ትንሣኤ በ፵ኛው ቀን)
10ኛ) ሰኔ 12 ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል (ሰኔ ሚካኤል)
11ኛ) ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕርገት በዓል መታሰቢያ (ዕርገታ ለማርያም)
ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ (ጳጳስ ዘደቡብ ኢትዮጵያ) አማካኝነት ሲሆን መቃኞዋ በ1916 ዓ.ም ተተክሎ አሁን ላለችው ቤተ መቅደስ በ1918 ዓ.ም መሠረት ጥለው በ1921 ዓ.ም ለአገልግሎት ክፍት አድርገው እስካሁን ድረስ ከዘጠኝ ዐሠርት ዓመታት በላይ አባቶች ካሕናት እያመሰገኑባት፤ ሊቃውንት አባቶች እየዘመሩባት፤ ምዕመናን እየተገለገሉባት ያለችውን ሕንጻ ቤተክርስቲያን አነጿት። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፦ በ1921 ዓ.ም በመጀመሪያ ግብጽ ካይሮ ሄደው ከተሾሙት አራት ጳጳሳት ውስጥ፤ በሕመም ምክንያት ሳይሄዱ ቀርተው የነበሩና፤ በኋላም የእስክንድርያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሐንስ በ1922 ዓ.ም ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ፤ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ በኾነችው፤ በታሪካዊቷ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን፤ ጥር 1 ቀን አምስተኛ ኾነው የተሾሙ አባት ሲሆኑ የመጀመሪያ ስማቸው እጨጌ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን በኋላ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ ዘደቡብ ኢትዮጵያ ተብለዋል። እርሳቸውም ፦ እርሱን ብርሃን ስንል እሷን እመ ብርሃን በምንላት እናቱ፤ እሱን አምላክ ስንል እሷን ወላዲተ አምላክ ብለን በምንጠራት ወላዲቱ፤ እሱን ሕይወት ስንል እሷን እመ ሕይወት እያልን ስሟን በውዳሴያችን በምናነሳሳት ሐጻኒቱ፤ በእጆቹ አበጃጅቶ የሰራን አምላካችን፤ ከድቅድቁ ጨለማ ያወጣን ብርሃናችን፤ ለኛ ሲል ሞቶ ሕይወታችን የኾነ ጌታችን፤ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሳለ የሰጠን እናታችን፤ እኛም በሐዋርያው በቅዱስ ዮሐንስ በኩል ከመስቀሉ ስር ኾነን የተቀበልናት አማላጃችን፤ የባሕርያችን መመኪያ የእግዚአብሔር እናቱ፤ የመዳናችን ምክንያት የአዳም ሕይወቱ በኾነችው በእመቤታችን በቅድስት_ድንግል_ማርያም በልደቷ መታሰቢያ ያነጿት ደብር ናት።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
ኢሜል
teklesawiros01@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
ልደታ • አዲስ አበባ
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ