Blogs & Articles

​🌼 ልዩ የአመቱ ማጠቃለያ እና የአዲስ አመት መቀበያ ልዩ የበገና ዝማሬ አዳር መርሃ ግብር 🌼
Active
ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
​🌼 ልዩ የአመቱ ማጠቃለያ እና የአዲስ አመት መቀበያ ልዩ የበገና ዝማሬ አዳር መርሃ ግብር 🌼
« እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ። » (መዝሙረ ዳዊት 70:22) ​ 🌼 ልዩ የአመቱ ማጠቃለያ እና የአዲስ አመት መቀበያ ልዩ የበገና ዝማሬ አዳር መርሃ ግብር 🌼 ​የአቃቂ ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የፍኖተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት 5ኛውን ዙር የአመቱ ማጠቃለያ እና የአዲስ አመት መቀበያ በማስመልከት ልዩ የበገና ቤተሰብ የበገና ዝማሬ አዳር መርሃግብር አዘጋጅቶላችኋል። ​በዚህ መንፈሳዊ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የአመቱን በረከት እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል። ​📅 ቀን፦ ነሐሴ 30 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ 📍 ቦታ፦ በሰንበት ትምህርት ቤታችን አዳራሽ ​ ይምጡ፤ በዝማሬ ታንፀው የአዲሱን ዓመት በረከት በምስጋና ይቀበሉ! ​#የበገና_ዝማሬ #ፍኖተ_ጽድቅ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት #አቃቂ_ፋንታ #የአዲስ_አመት_መቀበያ ✝️ አቃቂ ፋንታ ደብረ ፅጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን  ፍኖተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት ✝️
እንኳን ለገናናው ሊቀመላእክት ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊው ክብረበዓል በሰላም አደረሳችሁ
Active
ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
እንኳን ለገናናው ሊቀመላእክት ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊው ክብረበዓል በሰላም አደረሳችሁ
እንኳን ለገናናው ሊቀመላእክት ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊው ክብረበዓል በሰላም አደረሳችሁ ❖ "ፈዋሹና አስደሳቹ መልአክ፦ ቅዱስ ሩፋኤል" ❖ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ስሙ "የእግዚአብሔር ፈውስ" ወይም "እግዚአብሔር ይፈውሳል" ማለት ነው። ​"በጸሎቱ ለቅዱስ ሩፋኤል፤ ትድኅን ነፍስ እምደዌሃ ወሥጋሃሰ ይረክብ ፈውሰ።" (በቅዱስ ሩፋኤል ጸሎት ነፍስ ከደዌዋ ትድናለች፣ ሥጋም ፈውስን ያገኛል።) ዛሬም እኛ በሕይወት ጉዟችን ላይ ስንደክም፣ በበሽታና በጭንቀት ስንሰቃይ የቅዱስ ሩፋኤል ምልጃና ጥበቃ አይለየንም። ፈዋሹ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሕመማችንን ይፈውስልን፣ መንገዳችንን ይባርክልን! ​"በጸሎቱ ለቅዱስ ሩፋኤል፤ ትድኅን ነፍስ እም ማንም ሰው የማይቀርበት ጳግሜ 3/2018ዓ.ም ልዩ ዓመታዊው የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊው ክብረ በዓል  በአቃቂ ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ።
🌿በዓለ ንግሱ ለቅዱስ ሩፋኤል🌿
Active
ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
🌿በዓለ ንግሱ ለቅዱስ ሩፋኤል🌿
✨✨ታላቅ በዓለ ንግስና ጉባኤ ጥሪ✨✨✨ 🌿🌿🌿🌿ጳግሜ3🌿🌿🌿🌿 🌿በዓለ ንግሱ ለቅዱስ ሩፋኤል🌿 ቅዱስ ሩፋኤል ማለት:- ሩፋ-ሐኪም ኤል-እግዚአብሔር ሩፋኤል ማለት እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው ማለት ነው፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሸመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” ሄኖክ  6፡3 “አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሐዱ እምነ ሰብአቱ ሊቃነ መላእክት፡፡” ጦቢት 12፡15 በራማ ሰማይ ነገደ መናብርትን ይመራቸዋል፡፡ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ …፡፡”   “በራማ ሰማይ የሚገኘውን 10ሩን ነገደ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ እነዚህም ረቂቃን የሆኑ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲሆኑ በራማ በሁለተኛው ክፍል አስፍሯቸዋል፡፡” እግዚአብሔርን ማመስገን፡፡ “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ፡፡”            “አሸናፊ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገን ምስጋናህ በሳማይና   በምድር የመላ ነው፡፡” “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሠራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ  ወወሀቦሙ ማእጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት እግዚአብሔር ከሠራዊተ ሩፋኤል 24 ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል ካህናተ ሰማይ ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል የብርሃን ዘንግ ማህተሙ መስቀል የሆነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል፡፡” ራእይ 4፡45 ሕዝ 1፡11 ሩፋኤል ፡ ሆይ ፡ መንፈሳዊ ፡ ሐኪም ፡ ነህና ፡ ደዌ ፡ ኃጢአት ፡ እንዳያሰቃየን ፡ ፍቱን ፡ መድኃኒትህን ፡ ቀብተህ ፡ አድነኝ ፡ አቤቱ ፡ የሀብተ ፡ ረድኤትህም ፡ ተሳታፊ ፡ አድርገኝ።        ✨✨ መልክአ ሩፋኤል✨✨   🛑እንኳን  አደረሳችሁ አደረሰን፡፡🛑 ✝️ ፋንታ ደብረ ፅጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት✝️
አመታዊው የቅዱስ ሩፋኤል አከባበር በፎቶ
Active
ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም
አመታዊው የቅዱስ ሩፋኤል አከባበር በፎቶ
የአቃቂ ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን