Sunday SchoolActive

ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም

MIRAFE KIDUSAN ABUNE GEBREMENFES KIDUS AND ABUNE AREGAWI GEDAM

ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት

የሰንበት ት/ቤቱ ጠንካራ መገለጫዎች መካከል       ያጋጠሙ ችግሮችን በራስ ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ       የእርስ በርስ ተከባብሮ ተናብቦ መስራት       የጋለ የአገልግሎት ፍቅር መኖር

06 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ
1974 ዓ.ም
MIRAFE KIDUSAN ABUNE GEBREMENFES KIDUS AND ABUNE AREGAWI GEDAM
MIRAFE KIDUSAN ABUNE GEBREMENFES KIDUS AND ABUNE AREGAWI GEDAM

Sunday School

MIRAFE KIDUSAN ABUNE GEBREMENFES KIDUS AND ABUNE AREGAWI GEDAM

06 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

የቤተ ክርስቲያን ዶግማ ፣ቀኖናና ትውፊት ሳይለወጥ ሳይበረዝ በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ
ትውልዱን ከቤተክርስቲያኒቷ የማንነት መገለጫ አስተምህሮዎች የሚያስወጡ የየዘመናቱን ኢ-ክርስቲያናዊ ለውጦች በመከታተል በመቅረጽ
ጠንካራ የማሕበራዊ ሕይወት እና ኃላፊነቱን የሚወጣ፣ታማኝ አገልጋይ ፣ በጎ አርዓያነት ያለው ትውልድ በማፍራት

የእኛ ራእይ

ምእመናን በነገረ ሃይማኖት ትምህርት ልቀው የተሟላ ሰብእና ይዘው አርዓያነት ያላቸው ዘመንን የሚዋጁ ጉልህ ሃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ድርሻ የሚወስዱ አባቶቻቸውን የሚተኩ ሆኖ ማየት፡፡

የእኛ እሴቶች

Ø  ፈሪሐ እግዚአበሔር

Ø  ዘመኑን መዋጀት

Ø  በሃይማኖት መኖር

Ø  በፍቅር ማገልገል

Ø  ቁርጠኝነት

Ø  በጎ አርዓያ መሆን

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም

ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

የተመሰረተበት ቀን 1974 ዓ.ም ነሐሴ 5 ሲሆን የድሮ የሠንበት ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በፊት ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ ሳያልቅ በቤተልሔም ጀርባ ምድር ቤት ሲሆን ቤተክርስቲያኑ ሲመረቅ በታችኛው በር መውጫ ጫፍ ላይ ያለችው ቆርቆሮ ቤት ነበር ፡፡

ስለ እኛ

የሰንበት ት/ቤቱ ጠንካራ መገለጫዎች መካከል

•      ያጋጠሙ ችግሮችን በራስ ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ
•      የእርስ በርስ ተከባብሮ ተናብቦ መስራት
•      የጋለ የአገልግሎት ፍቅር መኖር

ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

• የምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ህይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክየሚገኘው በአዲስ አበባ አስተዳደር ክልል በቀድሞ አጠራር ከፍተኛ 19 ቀበሌ 55 በአሁኑ ደግሞ ቀበሌ 12/13 ክልል ውስጥ ወደ ደብረዘይት ስንወርድ በስተግራ በሚታጠፈው መንገድ ነው።
• ቤተክርስቲያኑ የተሰራው በተንጣለለ ሜዳ በ37000 ካሬ ሜትር ቦታ ሥፋት ዙሪያ ላይ ሲሆን በምስራቅ ወደ አቃቂ የሚወርደው የቀበና ወንዝ በምዕራፍ የቁጠባ ቤቶች እንደዚሁ በደቡብ አደባባይ አስፋልት መንገድ የሚያዋስኑት ስፍራ በስተ ሰሜን ምስራቅ የአባታችን አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ ተተክሏል፡፡ የአተካከሉን ሂደት በተመለከተ ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያዊ ጉዞአቸውን በመላእክት መሪነት ወደ ኢትዮጵያ በማድረግ በመጀመሪያ አክሱም ጽዮንን ጎበኙ ከዚያም ወደ ላስታ/ሩሃ/ መጥተው ቅዱስ ላሊበላ የጻድቁን ሁኔታና ቁመናቸውን አይቶ አደነቀ፡፡ ከእሱ ጋር ሊቀመጡ መስሎት በጣም ተደሰተ። ቅዱስ ላሊበላ ከአባታችን ጋር ስለ መንፈሳዊ ሕይወቱ ብዙ ተወያይተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ላሊበላ የጻድቁን አቋምና ላህይ በንጽህናና በቅድስና ያሸበረቁ ጻድቅና እውነተኛ አባት መሆናቸውን በትክክል ስለተረዳ ልዩ ስፍራ አዘጋጅቶላቸው አብረው ቢቀመጡ የተትረፈረፈ በረከት እንደሚያገኝ ስላመነ አባቴ ክእኔ ጋር ቢቀመጡስ? ብሎ ጠየቃቸው አባታችን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስም የእኔ መኖሪያ በዚህ አይደለም፡፡
• በደቡብ ኢትዮጵያ ዝቋላ እየተባለ በሚጠራው ተራራ ላይ ነው ብለው መለሱለት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከላስታ ወደ ዝቋላ ሲደርሱ ቅዱስ ላሊበላ ከታማኝ አሽከሮቹ ጋር ተከተላቸው በጉዞአቸው ላይ እንደሐዋርያው ያዕቆብ በዚህ ደብር ፀሐይ ጠለቀችባቸው አዳራቸውንም አሁን ቤተክርስቲያኑ በተተከለበት በዚሁ ስፍራ አደረጉ በዛ ሌሊት ሁለቱም ቅዱሳን በየአረፉበት ስፍራ ሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ አደሩ፡፡ በነጋታው ተገናኝተው ሲወያዩ አባታችን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ በዚህ ስፍራ በስማቸው ፀበል እንደሚፈልቅና ብዙ ሕሙማን ነፍስና ቁስላነ ሥጋ እንደሚፈወሱበት ተብየዋል፡፡ ቅዱስ ላሊበላም በበኩሉ በዚህ ስፍራ እንደሰማይ ከዋክብት እንደባሕር አሸዋ የበዙና የአባታችን አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ የሀጋ ልጆች ነን እያሉ ሲዘምሩና ልዑል እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ አየሁ ብሎ ተናገረ። ሁለቱም ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ አድንቀው ጉዞአቸውን ወደ ዝቋላ ቀጠሉ እነሆ ዛሬ ይህ ቦታ /ቤተክርስቲያን/ በአባታችን በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም ፀበል ፈልቆ በፀበሉም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ ይገኛሉ፡፡ የሁለቱ ቅዱሳን ራዕይ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ - ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣም ዳሩ ግን ከእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ተናገሩ" 2ኛ ጴጥ ም.1 ቁ. 21 ከሰው መርጦ ለሹመት ከእንጨት ተመርጦ ለታቦት እንዲሉ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና የቅዱስ ላሊበላ ትንቢታዊ ቃል ስምሮ የካቲት ወር 1974 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የመሠረተ ድንጋይ ተጣለ፡፡
• ሐምሌ 27 ቀን 1974 ዓ.ም መቃኞው ተሰርቶ በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማ መቃኞው ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ የቤተክርስቲያኑ ህንፃ ግንባታ መስከረም 19 ቀን 1978 ዓ.ም መሠረት ተጥሎና ሥራው ተጀምሮ፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 1983 ዓ.ም የምርቃቱ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሞአል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የጻድቁ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ስምህን የጠራ፤ መታስቢያህን ያደረገ፣ በስምህ ቤተክርስቲያንህን የሠራ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም በመንግስተ ሰማያት ዋጋውን አላስቀረበትም ብለ‐ በሰጣቸው ቃል ኪዳን መሠረት ምዕመናን ጻድቁ በረገጡትና በፀለዩበት ስፍራ ቤተክርስቲያናቸውን እንዲሰሩ እግዚአብሔርፍቃዱ ሆኖ በዚህ ስፍራ ቤተክርስቲያናቸው ተተክሏል፡፡

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

ኢሜል

dave1asrat@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

06 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

MIRAFE KIDUSAN ABUNE GEBREMENFES KIDUS AND ABUNE AREGAWI GEDAM

Address

06 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ

Lat 8.94484Lng 38.77080
Open in Google Maps