
ጀሞ ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን
Felege jordan saint john the baptist, holy virgin mary church
ሰ/ት/ቤት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት የትምህርት ቦታ ነች፡፡ ቤተክርስቲያናችን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት ስታካሒድ ኖራለች፤ ሰ/ት/ቤታችንም ከተመሰረ…


Sunday School
Felege jordan saint john the baptist, holy virgin mary church
ጀሞ 01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
ጀሞ ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።
<p>የሰንበት ትምህርት ቤቱ ተልእኮ በማቴ 28፥19 “እንግዲህ ሂዱና በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፡፡” የሚለውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ትምህርተ ወንጌልን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለሕፃናት፣ ለወጣቶች እንዲሁም ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ተተኪዎችን ማፍራት ነው፡፡ </p>
<p>‹‹ህፃናት ወደኔ ይመጡ ዘንድ ተዋቸዉ አትከልክሏቸው›› ማቴ 19፤14 ‹‹የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› መክ 12፤1 ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ በተፃፈዉ መሠረት ህፃናትና ወጣቶች ሁሉ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት በጥበብና በሞገስ እንዲያድጉ ማድረግ፡፡</p>
<p>እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሰውን ማክበር፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ፣ ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣ ዘመኑን መቅደም መዋጀት</p>
ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
ጀሞ ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን
ፍኖተ ሠላም ሰንበት ት/ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
ሰ/ት/ቤት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት የትምህርት ቦታ ነች፡፡ ቤተክርስቲያናችን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት ስታካሒድ ኖራለች፤ ሰ/ት/ቤታችንም ከተመሰረተችበት 1996 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ዘርፍ ወጣቱን ከሕፃንነቱ ጀምሮ በማስተማር ለሰው ልጅ በሚያፈልጉት የአአምሮና የመንፈስ እድገት የተሟላ እንዲሆኑ ስትሠራ በተጨማሪም ማህበራዊ ግዴታዎቿን በመወጣት ላይ ትገኛለች

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
+251938040506
ኢሜል
fnoteselamsundayschool@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
ጀሞ 01 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ