Sunday SchoolActive

የካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን

Kara Kore Mezgebe Mhiret KIdus Fanuel Church

ሐመረ ኖኅ ሰንበት ትምህርት ቤት

ወንድሞች በብረት ቢሆኑ እነሆ ያማረ የተዋበም ነው። መዝ፡፻፴፪፥፩

11 • Kolfe Keranio • Addis Ababa
1993 ዓ.ም
+251911223344
Kara Kore Mezgebe Mhiret KIdus Fanuel Church
Kara Kore Mezgebe Mhiret KIdus Fanuel Church

Sunday School

Kara Kore Mezgebe Mhiret KIdus Fanuel Church

11 • Kolfe Keranio • Addis Ababa

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

የካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

<p>&nbsp;ስለ ሃይማኖታቸው በቂ እውቀት ያላቸው አባላት እና የነገይቱ ቤተክርስቲያን ተተኪ አገልጋዮችን ማፍራት፡፡&nbsp;</p>

የእኛ ራእይ

<p>የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን እምነትና ስርዓት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጣቱን ትውልድ አደራጅቶ ሰማያዊ ርስት የሚወርስበትን ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም እንዲዳረስ ማድረግ፤ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ ቀኖና እና ትውፊት ጠብቆ እና አስጠብቆ በአበው እግር ተተኪ እንዲሆን ማድረግ፤ የቤተክርስቲያን ልጆችን በቀደመች እምነታቸው እንዲጸኑ ማስቻል ነው፡፡</p>

የእኛ እሴቶች

<p>ቅዱስና ምሳሌ የሆነ አገልግሎት ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣&nbsp;በፍቅር የሆነ አገልግሎት፣&nbsp;ዘመኑን መቅደም ፣&nbsp;ክርስቲያናዊ&nbsp; ኃላፊነት</p>

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

የካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን

ሐመረ ኖኅ ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

በአህዛብ የተከበበው መንደራቸውና መንፈሳዊት ማዕድን የተጠማች ነፍሳቸው እረፍት የነሷቸው የወታደር ሰፈር ምዕመናን ነፍሳቸውን ወደ ሕይወት ምንጭ ታደርሳቸው ዘንድ ሐመረ ኖኅ የተሰኘች የጸሎት ማህበር መሰረቱ። ማህበሩ የአካባቢውን ህጻናትና ወጣቶች በማሰባሰብና ቆብ በማስለበስ ከአጥቢያ ደብራት ጋር በጋራ በመሆን የ1992ን ጥምቀት በጋራ እንዲያገለግሉ አደረጉ። የማኅበሩ አባላት ፈቃደ እግዚአብሔር ሳይሆን ቀርቶ በዶዘር ፈርሶ የነበረውን ቤ/ን በጊዜው ብዙ ዋጋ በመክፈልና በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር 9 1993 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው የቅዱስ ፋኑኤልን ታቦት አስገቡ። ታዲያ ከደብሩ ምስረታ በፊት በጥምቀት በዓል ሲያገለግሉ የነበሩት ወጣቶችና ሕጻናት በጋራ በመሆን የደብሩን ሰ/ት/ቤት በማቋቋም የቀደመ ስያሜያቸውን በማስጠበቅ ሐመረ ኖኅ ብለው አገልግሎታቸውን ቀጠሉ።

ስለ እኛ

ወንድሞች በብረት ቢሆኑ እነሆ ያማረ የተዋበም ነው። መዝ፡፻፴፪፥፩

የካራ ቆሬ መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

በአህዛብ የተከበበው መንደራቸውና መንፈሳዊት ማዕድን የተጠማች ነፍሳቸው እረፍት የነሷቸው የወታደር ሰፈር ምዕመናን ነፍሳቸውን ወደ ሕይወት ምንጭ ታደርሳቸው ዘንድ ሐመረ ኖኅ የተሰኘች የጸሎት ማህበር መሰረቱ። የአከባቢው ምዕመናን በአከባቢያቸው ቤ/ን ለማስተከል  በ1989 ዓ.ም አሁን መስቀል ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ የቅዱስ ፋኑኤልን ቤ/ን አንጸው ጽላት እስከማስገባትና ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና ምዕመናንን ለምረቃ እስከመጥራት  ደርሰው በአህዛብና በጸጥታ ኃይሎች ሰፍራው ተከቦና ለማለፍ ተከልክለው ፤ በሚይሳዝንም ሁኔታ ቤ/ኗ በዶዘር እስከመፍረስ በመድረሱ  ፈቃደ እግዚአብሔር ሳይሆን ቀርቶ ፈርሶ የነበረውን ቤ/ን በማኅበሩ አባላት በተነሳ በጊዜው ብዙ ዋጋ በመክፈልና በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር 9 1993 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው የቅዱስ ፋኑኤልን ታቦት አስገቡ። 

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251911223344

ኢሜል

hamer.nohe03@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

11 • Kolfe Keranio • Addis Ababa

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

Kara Kore Mezgebe Mhiret KIdus Fanuel Church

Address

11 • Kolfe Keranio • Addis Ababa

Lat 8.99111Lng 38.66473
Open in Google Maps