Sunday SchoolActive

የቦሌ አየር ማረፊያ ወረገኑ ደ/ገ/ቅ/በአታ ለማርያም እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ

Bole Airport Weregenu D.Genet St. Beata LeMariam & Abune Teklehaymanot church

ፍኖተ አበው ሰንበት ትምህርት ቤት

በዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ ከበሮና የአገልግሎት ልብሶችን (ልብሰ ሰብሐት) ማሟላት ተቻለ። ቀጥሎም ከባለመሬቶች ጋር በተደረገ የውል ስምምነት ቦታ ተገኝቶ የአዳራሽ ግንባታ ተጀመረ። በወቅቱ በአዲስ አበባ ዳርቻ ከነበረው የቤቶች ፈረሳ ቆርቆሮዎችን በቅናሽ በመግዛት ጣሪያው ተመታ። ነገር ግን የገቢ እጥረት ግንባታውን አገደው። በዚህ ጊዜ አባላቱ በታላቅ ተጋድሎ ከአቅራቢያው ወንዝ አሸዋ

12 • ቦሌ • አዲስ አበባ
2014 ዓ.ም
+251900653068
Bole Airport Weregenu D.Genet St. Beata LeMariam & Abune Teklehaymanot church
Bole Airport Weregenu D.Genet St. Beata LeMariam & Abune Teklehaymanot church

Sunday School

Bole Airport Weregenu D.Genet St. Beata LeMariam & Abune Teklehaymanot church

12 • ቦሌ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

የቦሌ አየር ማረፊያ ወረገኑ ደ/ገ/ቅ/በአታ ለማርያም እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

<p>የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፣ቀኖና እና ትውፊት አውቆ የሚያሳውቅ ጠብቆ የሚያስጠብቅ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጠንካራ የሆነ በመንፈሳዊ ትምህርትም በዘመናዊ ትምህርትም የበሰለ በሃይማኖት እና በምግባር የታነጸ ትውልድ ማየት</p>

የእኛ ራእይ

<p>የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት እና ሥርአት ተጠብቆ ሳይለወጥ ሳይበረዝ በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ</p><p>ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል የሆነ ክርስቲያን ሁሉ ሃይማኖቱን እና የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅ እንዲረዳ ማድረግ</p>

የእኛ እሴቶች

<p>እግዚአብሔርን መፍራት ፣&nbsp; ወጣቶችን እና ሕጻናትን በቃለ ወንጌል ማነጽ ፣ ትህትና ፣ ሰውን ማክበር ፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት ፣&nbsp; ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣ ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት</p>

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

የቦሌ አየር ማረፊያ ወረገኑ ደ/ገ/ቅ/በአታ ለማርያም እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ

ፍኖተ አበው ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

የፍኖተ አበው ሰንበት ትምህርት ቤት ህዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም በጥቂት ብርቱ አባላት ተመሰረተ። በጅማሮው ወቅት የመማሪያ አዳራሽ ባለመኖሩ፣ አባላቱ ከቤተክርስቲያኑ ጀርባ በሚገኝ ዛፍ ስር በመጠለል ፀሐዩን፣ ብርዱንና ዝናቡን እየተቋቋሙ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ነበር። ይህንን የቦታ ችግር ለመፍታት ሰኔ 05 ቀን 2014 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ ቢደረግም፣ ከታሰቡት 35 ሰንበት ትምህርት ቤቶች መካከል የተገኙት ሁለት ደብራት ብቻ በመሆናቸው ስራው እንደታቀደው ሳይሳካ ቀርቷል። ሆኖም አባላቱ ተስፋ ሳይቆርጡ በአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ፣ በደብረ ታቦር (ቡሄ) እና በአዲስ ዓመት በዓላት ገቢ ማሰባሰብ ጀመሩ።&nbsp;

ስለ እኛ

በዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ ከበሮና የአገልግሎት ልብሶችን (ልብሰ ሰብሐት) ማሟላት ተቻለ። ቀጥሎም ከባለመሬቶች ጋር በተደረገ የውል ስምምነት ቦታ ተገኝቶ የአዳራሽ ግንባታ ተጀመረ። በወቅቱ በአዲስ አበባ ዳርቻ ከነበረው የቤቶች ፈረሳ ቆርቆሮዎችን በቅናሽ በመግዛት ጣሪያው ተመታ። ነገር ግን የገቢ እጥረት ግንባታውን አገደው። በዚህ ጊዜ አባላቱ በታላቅ ተጋድሎ ከአቅራቢያው ወንዝ አሸዋ በማውጣትና ድንጋይ በመልቀም በጉልበታቸው ተሸክመው አመጡ። በዚህ እልህ አስጨራሽ ጥረትና መስዋዕትነት ዛሬ የሚታየው አዳራሽ ተገንብቶ ለታሪክና ለአገልግሎት በቅቷል።

የቦሌ አየር ማረፊያ ወረገኑ ደ/ገ/ቅ/በአታ ለማርያም እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

የቦሌ አየር ማረፊያ ወረገኑ ደ/ገ/ቅ/በአታ ለማርያም እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ 2014 ዓ.ም ተመሰረተ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251900653068

ኢሜል

test@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

12 • ቦሌ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

Bole Airport Weregenu D.Genet St. Beata LeMariam & Abune Teklehaymanot church

Address

12 • ቦሌ • አዲስ አበባ

Lat 8.97823Lng 38.82104
Open in Google Maps