ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ወመካነ ጎሎጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
St. Yohannes (Wolde Negodguad) Church
ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤታችን የአዲስ አበባ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የሚገኘው በከተማዋ ማዕከላዊ ቦታ ከፒያሳ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተነሥቶ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በሚወሰወደው መንገድ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በ3.6 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው በከተማዋም በሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ስም የተሰየመ ብቸኛ ቤተ ክር…

Sunday School
St. Yohannes (Wolde Negodguad) Church
04 • አራዳ • አዲስ አበባ ኢትዮጵያ Addis Ababa Ethiopia. ከፒያሳ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ከሰባራ ባቡር አለፍ ብሎ ባለው አካባቢ ይገኛል ።
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ወመካነ ጎሎጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፣ቀኖና እና ትውፊት አውቆ የሚያሳውቅ ጠብቆ የሚያስጠብቅ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጠንካራ የሆነ በመንፈሳዊ ትምህርትም በዘመናዊ ትምህርትም የበሰለ በሃይማኖት እና በምግባር የታነጸ ትውልድ ማየት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት እና ሥርአት ተጠብቆ ሳይለወጥ ሳይበረዝ በቀጥታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ

ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል የሆነ ክርስቲያን ሁሉ ሃይማኖቱን እና የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅ እንዲረዳ ማድረግ

እግዚአብሔርን መፍራት ፣ ወጣቶችን እና ሕጻናትን በቃለ ወንጌል ማነጽ ፣ ትህትና ፣ ሰውን ማክበር ፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት ፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ ፣ ፅናትና ምስክርነት ፣ ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ወመካነ ጎሎጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤታችን
የአዲስ አበባ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የሚገኘው በከተማዋ ማዕከላዊ ቦታ ከፒያሳ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተነሥቶ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በሚወሰወደው መንገድ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በ3.6 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው በከተማዋም በሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ስም የተሰየመ ብቸኛ ቤተ ክርሰቲያን ነው ፡፡

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
ይህ አሁን የሚገኘው የቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ከመሠራቱ አስቀድሞ ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ እና ብላታ ተሰማ ደባልቄ አሻሽለው ለመሥራት ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጥያቄ ቢያቀርቡም ንጉሡ እራሳቸው ሊሰሩት ስለፈለጉ ሳይፈቅዱላቸው ቀርተዋል።
በኋላ ግን የእግዚአብሔር ጊዜ ደርሶ ልዑል መኮንን ግንቦት 4 ቀን 1949ዓ.ም በድንገት ዐረፉ።
ልዑሉ የተወለዱት ጥቅምት 4 ቀን 1916 ዓ.ም በመሆኑ ዕረፍታቸውም ልደታቸውም በቅዱስ ዮሐንስ ዕለት መሆኑን የተመለከቱት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለልጃቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድ አዲሱ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በፍጥነት እንዲሠራ ስላዘዙ ግንቦት 4 ቀን 1950 ዓ.ም ሕንጻው እንዲጀመር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠው በ1961ዓ.ም በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ተባርኮ ንጉሱ በተገኙበት ለአራተኛ ጊዜ ታቦቱ አሁን ወዳለው ቤተ መቅደስ ገብቷል።.
በጊቢው ውስጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መቅደስ ያለ ሲሆን ብዙዎች በቅርብ ሆነ በሩቅ ያሉ ምእመናን ፈውስ እና በረከት ለማግኘት የሚጠመቁባቸው አሥራ አራት የተለያዩ ጠበሎች ያሉበት ቤተ ሳይዳ የተሰኘ የጠበል ቦታም ከቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ በድሮ አጠራር ከፍተኛ 1 ቀበሌ 03 የሚገኝ ሲሆን አሁን በአራዳ ክፍለ ከተማ ከፒያሳ መናገሻ ገነተ ጽጌ (አራዳ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ተነሥቶ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ ወደ አስኮ በተዘረጋው የአርበኞች መንገድ በራስ ደስታ ሆስፒታል አካባቢ ይገኛል ከመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የ3.6 ኪ ሜ ርቀት ያለው ሲሆን ስሙ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ መባሉ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ( የነጎድጓድ ልጅ ) ተብሎ ስለሚጠራ ነው ፡፡ የሉቃ 9፡51 – 56
የቅዱስ ዮሐንስ ታቦት አመጣጥ
የፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ታቦት ከአፄ ዮሐንስ ዘንድ ነበረ እርሳቸውም ለንጉሥ ሚካኤል ሰጡት ንጉሥ ሚካኤልም ሰገሌ ላይ ሲማረኩ ታቦቱን ይዘውት መጥተው ስለነበር በንግሥት ዘውዲቱ ትእዛዝ ታቦቱ አዲስ አበባ በሚገኘው አራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በደባልነት ገብቶ ተቀመጠ። ንግሥቲቱም ምኞታቸው ከፍተኛ ቤተ ክርስቲያን ማሠራት ስለነበር ለጊዜው ደህና ቦታ ተፈልጎ መቃኞ እንዲሠራለት ለቤተክርስቲያን ባለስልጣናት ትዕዛዝ ሰጡ። በዚሁ መሰረት ታቦቱ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ቦታ አርፎ ነበር ዋና ዋናዎቹም ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
ኢሜል
fikureegzi4@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
04 • አራዳ • አዲስ አበባ ኢትዮጵያ Addis Ababa Ethiopia. ከፒያሳ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ከሰባራ ባቡር አለፍ ብሎ ባለው አካባቢ ይገኛል ።
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ
Address
04 • አራዳ • አዲስ አበባ ኢትዮጵያ Addis Ababa Ethiopia. ከፒያሳ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ከሰባራ ባቡር አለፍ ብሎ ባለው አካባቢ ይገኛል ።