Sunday SchoolActive

ቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን

KALITY MEKANE SELAM SAINT ARSEMA AND SAINT RUFAEL CHURCH

ፈለገ ሰማዕት ሰንበት ትምህርት ቤት

በ2014ዓ.ም ከዚህ ቀደም በነበረው ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ተማሪዎችን በሶስት ክፍል ማለትም ቂርቆስ፣እስጢፋኖስ እና ቀዳማይ ብሎ በመክፈል ትምህርት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን 2015ዓ.ም እንደአዲስ የነበረውን መደበኛ ትምህርት በማጠናከር ከ130 በላይ ተማሪዎችን በመመዝገብ ትምህርት በመስጠት ከ59 በላይ ተማሪዎችን በሰርቲፊኬት ማስመረቅ ተችሏል፡፡ በ2017ዓ.ም ከ28 በላይ መምህራን

05 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ
2013 ዓ.ም
+251961138753
KALITY MEKANE SELAM SAINT ARSEMA AND SAINT RUFAEL CHURCH
KALITY MEKANE SELAM SAINT ARSEMA AND SAINT RUFAEL CHURCH

Sunday School

KALITY MEKANE SELAM SAINT ARSEMA AND SAINT RUFAEL CHURCH

05 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

ቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

የእኛ ራእይ

በመንፈሳዊ ሕይወት የጎለመሱ በምግባርና በሃይማኖት የታነጹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰውን የሚያከብሩ የሰንበት ት/ቤት አባላት ማፍራት

የእኛ እሴቶች

፩  አገልጋይነት

፪  ቅንነት

ሀ. ሰ/ት/ቤቱ ቅን አስተሳሰብ ለተሟላ አገልግሎት አሰጣጥ መሠረት መሆኑን ያምናል

፫ ታማኝነት

፬  አሳታፊየአሠራርባህል

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

ቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን

ፈለገ ሰማዕት ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

የፈለገ ሰማዕት ሰንበት ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት በቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ልዩ ስሙ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ወይም ውሃ ልማት ኢንዱስትሪ ሠፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የምትገኝ ሰንበት ትምህርት ቤት ናት፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያዘው መሠረት አባቶችና ካህናትን በመጠየቅ እንዲሁም ከተለያዩ ደብራት መረጃን በመጠየቅ ሰኔ 26/2013ዓ.ም ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገ ሰማዕት ተብላ ልትቋቋም ችላለች፡፡

ስለ እኛ

በ2014ዓ.ም ከዚህ ቀደም በነበረው ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ተማሪዎችን በሶስት ክፍል ማለትም ቂርቆስ፣እስጢፋኖስ እና ቀዳማይ ብሎ በመክፈል ትምህርት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን 2015ዓ.ም እንደአዲስ የነበረውን መደበኛ ትምህርት በማጠናከር ከ130 በላይ ተማሪዎችን በመመዝገብ ትምህርት በመስጠት ከ59 በላይ ተማሪዎችን በሰርቲፊኬት ማስመረቅ ተችሏል፡፡ በ2017ዓ.ም ከ28 በላይ መምህራን በመመደብ ከ264 በላይ ተማሪዎችን በመመዝገብ መደበኛ ትምህርት ማስተማር የጀመርን ሲሆን አሁን ላይ ከ209 በላይ ተማሪዎች ትምህርቱን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

ቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

የቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ልዩ ስሙ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ወይም ውሃ ልማት ኢንዱስትሪ ሠፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ለብዙ ዓመታት መቃኞ ቤተ ክርስቲያኗን ለመሥራት ጥረት እየተደረገ ከቆየ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1999 ዓ.ም በወ/ሮ ሙሉ ሮቤ 2165 ካሬ ሜትር ቦታ ለጋሽነት በእነ ቄስ ኑርልኝ ዘለዓለም እና በአካባቢው ምዕመናን እና  እግዚአብሔር በፈቀደላቸው ታላላቅ አባቶች አማካኝነት መቃኞ ቤተ ክርስቲያኑ ተሠርቶ ለ6 ወራት አገልገሎት ከሰጠች በኋላ በወቅቱ ከነበረው የመንግስት የፀጥታ አካላት ጋር ባለመግባባት ምክንያት ብዙ የአካባቢው ምዕመናን ድብደባና እንግለት ከደረሰባቸው በኋላ መቃኞ ቤተ ክርስቲያኑ ፈርሶ የአካባቢው ምዕመናንና በጊዜው የነበረው መሥራች ኮሚቴ በጋራ በመነጋገር በቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአደራ መልክ ፅላቱን ከንዋዬ ቅዱሳቱ ጋር እንዲቀመጥ አድርገዋል።

በድጋሜ ቦታውን ለማስከበርና ፅላቱ ወደ መቃኞ ቤተ ክርስቲያኑ እንዲመለስ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ሳይሳካ ለብዙ ዓመታት ቆይቶ በ2006 ዓ.ም በአዲስ ተጀምሮ አሁንም አገልግሎትን ለመስጠት እንቅስቃሴ ቢደረግም ለሁለተኛ ጊዜ በአፍራሽ ግብረ ኃይል ሊፈርስና አገልግሎቱ ሊቋረጥ ችሏል።

በመቀጠልም በዚህች ተአምረኛ ቤተ ክርስቲያን መፍረስ በጊዜው ያሳሰባቸው የአካባቢው ምዕመናንና በጊዜው የነበሩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሥራ አስኪያጅ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የተለያዩ የሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶችና የመንግሥት አካላት ቤተ ክርስቲያኗ ትተከል የሚል ደብዳቤ ቢፅፉም ሳይሳካ ለ15 ዓመታት ቆይቷል።

በመሆኑም ይሄንን ጉዳይ በድጋሜ በማጤን እና ቤተ ክርስቲያኗ መተከል አለባት የሚለውን እንደ መርህ በመያዝ እና ክርስቲያናዊ ግዴታችንን መወጣት አለብን በማለት እስከ ከንቲባ ጽ/ቤት ድረስ በመጓዝ ቤተ ክርስቲያኗ ባለመብትና ባለይዞታ እንድትሆን በካቢኔ ውሳኔ እንድታገኝ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ አባቶችና ወንድሞች እንዲሁም እናቶችም ጨምር የወቅቱ መስራች ኮሚቴ አባላት መልአከ ሰላም ሀዲስ ሐዋርያ ታረቀኝ፣ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ኪዳነ ማርያም፣መጋቤ ምሥጢር አደለኝ መሰለ፣ላዕከ ወንጌል ስማቸው መልኬ፣መጋቤ ሥርዓት ኑርልኝ ዘለዓለም፣ሊቀ ትጉሃን ቡሩክ ደሳለኝ በመሆን እና የአካባቢ ምዕመናንን በማስተባበር ማለትም ወ/ሮ ሀረገወይን ሽታ፣ወ/ሮ ሰላማዊት ወርቁ፣ወ/ሮ አረጋሽ መኮንን፣ወ/ሮ ማርያምቸር ደለለኝ፣ወጣት አካሉ፣አቶ ስምዖን ጴጥሮስ፣አቶ ሙሉጌታ ተሾመ እና ሌሎችም በስም ያልጠቀስናቸው ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን ፍቅር በልቦናቸው ያደረባቸው ምዕመናን እና በብፅዕ አባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ ቡራኬና ጸሎት እንዲሁም በክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ አጋዥነትና አባታዊ መመሪያ ሰጭነት በቤተ ክርስቲያኗ ስም ህጋዊ ካርታ ወጥቶላት ሰኔ 13/2013 ዓ.ም በአካባቢው ምዕመናን ቀናኢ አስተሳሰብ መቃኞ ቤተ ክርስቲያኑ በአጭር ቀናት ውስጥ ተሰርቶ ስደተኛዋ የቅድስት አርሴማ ፅላት ከ15 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከመካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በክብር ወደ ቀድሞ ቦታዋ ተመልሳለች።

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251961138753

ኢሜል

semaetfelege@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

05 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

KALITY MEKANE SELAM SAINT ARSEMA AND SAINT RUFAEL CHURCH

Address

05 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ

Lat 8.99587Lng 38.78504
Open in Google Maps