ቃሊቲ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል
kality anketse berehan kideset dengel maryam Catedralll
ሰንበት ት/ቤቱ በይፋ ከመመስረቱ በፊት ከቤተክርስቲያኑ ምስረታ ጀምሮ ወጣቶች ከህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ጋራ በጋራ በመሆን ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ያከናውኑ ነበር፡፡ ሐምሌ 14 ቀን 1994 ዓ.ም በቃለአዋዲ እና በስርአተ ቤተክርስቲያን መሰረት ወጣቶቹ ከቤተክርሰቲያኒቱ አስተዳዳሪ አባ ቃለአብ ጉዳይነህ ጋር በተባበር የሰ/ት/ቤቱu የመጀመሪያ ስራ አመራር እነዲመረጡ አደረጉ፡፡ በቤተክርሰ…

Sunday School
kality anketse berehan kideset dengel maryam Catedralll
08 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ
የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ
ቃሊቲ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

‹‹ሒዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችሁ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ፡፡›› ማቴ ፳፰፥፲፱ ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ወንጌልን አመቺ በሆነ መንገድ ሁሉ ለመላው ዓለም መስበክ፡፡

የዜማ መገልገያዎች ትምህርትን በክፍለ ከተማችን እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በስፋት እና በጥራት እንዲሰጥ ማድረግ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ሥርዓትና ትውፊት ተጠብቆ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ማፍራት፡፡

ጥንታዊ የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዜማ መሳሪያዎችን ትውፊታቸውን ጠንቅቆ የሚወውቅ እና የሚጠቀም አባል ማፍራት እንዲሁም ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ፡፡

ፍቅር, ደስታ, ሰላም, ትዕግሥት, ቸርነት, በጎነት, ታማኝነት, ጨዋነትና ራስን መግዛት

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ
ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ
ቃሊቲ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል
የቃሊቲ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል እመ-ብዙኃን ሰንበት ትምህርት ቤት
ስለ አመሰራረቱ
ስለ እኛ
ሰንበት ት/ቤቱ በይፋ ከመመስረቱ በፊት ከቤተክርስቲያኑ ምስረታ ጀምሮ ወጣቶች ከህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ጋራ በጋራ በመሆን ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ያከናውኑ ነበር፡፡
ሐምሌ 14 ቀን 1994 ዓ.ም በቃለአዋዲ እና በስርአተ ቤተክርስቲያን መሰረት ወጣቶቹ ከቤተክርሰቲያኒቱ አስተዳዳሪ አባ ቃለአብ ጉዳይነህ ጋር በተባበር የሰ/ት/ቤቱu የመጀመሪያ ስራ አመራር እነዲመረጡ አደረጉ፡፡
በቤተክርሰቲችን 4ተኛው አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ገብረ ዩሐነስ መልካም ፍቃድ አማካኝነት ሰንበት ት/ቤታችን እስካሁን ድረስ መጠሪያ የሆናትን እመ ብዘኃን የሚለውን ስያሜ አግኝታለች፡፡

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ
ቤተክርስቲያኒቱ ከመቆርቆሯ አስቀድሞ በቦታው የሚኖሩ አባቶች በተለያዩ ጊዜ ራዕይ እንደተገለጠላቸው ይናገራሉ፡፡
ለአብነት ያህል መንግስት በአካባቢው የቁጠባ ቤቶችን ለመገንባት መሃንዲሶችን ልኮ የቅየሳ ስራዎችን በሚሰራበት ወቅት አሁን ቤተክርስቲያኒቷ በተመሰረተችበት ቦታ ላይ ሲመለከቱ የቅየሳ መሳሪያው በተደጋጋሚ ከአገልግሎት ውጪ እየሆነ ቦታውን ለማየት ተቸግረዋል፡፡
ይህንን ተአምር በአይናቸው የተመለከቱ የመንግስት መሐንዲሶች ቦታውን ከመንካት ተቆጥበዋል፡፡
ቤተክርስቲያኒቷ እንድትታነፅ ጋሻ መሬታቸውን የሰጡ የእድሜ ባለጸጋ የሆኑት ጋሽ ደመሳ ዋቅጅራ ይባላሉ፡፡
የቤተክርስቲያኒቱ ግንባታ ነሐሴ 1993 ዓ.ም ተጀምሮ ጥር 18 1994 ዓ.ም 6 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠናቋል ፡፡
በዚህም ጥር 18 ቀን 1994 ዓ.ም ታቦተ ህጉ ገብቶ ጥር 19 ቀን 1994 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል ከ2 ቀን በኋላ ጥር 21 ቀን 1994 ዓ.ም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ንግስ ሆኑዋል ፡፡
በ2003 ዓ.ም የአዲሱ ሕንፃ ቤተክርስቲያን በብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል አማከካኝነት የመሰረተ ድንጋይ ተጥሎ ግንቦተ 20 ቀን 2016 ዓ.ም 5 ብፁአን አባባች በተገኙበት አዲሱ ቤተክርስቲያን በቅብዓሜሮን ከብሮዋል በዚሁ ቀንም ደብራችን በብፁዓን አባቶች መልካም ፈቃድ የቃሊቲ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴደራል የሚል መጠሪያ አግኝታለች በነጋታውም ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የአመቤታችን ክብረ አዓል በተደረገበት እለት ታቦተ ህጉ በፊት ከነበረበት ቤተመቅደስ ወጥቶ ወደአዲሱ ቤተመቅደስ ገብቷል፡፡
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ያግኙን
የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ
ስልክ
+251972853095
ኢሜል
eemebzuhansundayschool@gmail.com
ሁኔታ
Active
አድራሻ
08 • አቃቂ ቃሊቲ • አዲስ አበባ
ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ
Location
አካባቢ