Sunday SchoolActive

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

Debre Bisrat Kidus Gebriel Church

አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት

ሰንበት ትምህርት ቤቱ 10 ዋና ዋና ክፍላትና 35 ንዑስ ክፍላትን (የስራ ቡድኖች) በመያዝ የተለያዩ የሰንብት ትምህርት ቤት አገለግሎቶች ይሰጣል፡፡

8 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
1959 ዓ.ም
+251911683572
Debre Bisrat Kidus Gebriel Church
Debre Bisrat Kidus Gebriel Church

Sunday School

Debre Bisrat Kidus Gebriel Church

8 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

<p>ለመንግሥተ ሰማያት የሚያበቃ ሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በሁሉም የትምህርት ማስተላለፊያ መንገዶች ማስተማር የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ጠብቆ ማስጠበቅ እንዲሁም አባላት በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩቶ በማሳደግ የነገይቱ ቤተክርስቲያን ተረካቢ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡&nbsp;</p>

የእኛ ራእይ

<p>ቅዱሳን አባቶች ጠብቀው ያስረከቡንን የቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት አክብሮና አስከብሮ ተስፋ የምናደርገውን መንግሥተ ሰማያት ለመውረስ የሚያበቃ የጸና ሃይማኖትና ምሳሌ የሆነ ምግባር ይዞ የሚገኝ ጥበበኛ ትውልድን የሚያፈራ ሰንበት ትምህርት ቤት ተፈጥሮ ማየት፡፡</p>

የእኛ እሴቶች

<p>ሰንበት ትምህርት ቤቱም ሆነ አባላቱ እጅግ የከበረ ዋጋ የሚሰጡት ከምንም ነገር የሚያስቀድሙት መገለጫዎች፦</p><p>መንፈሳዊነት፣አክባሪነት ፣አገልጋይነት ፣የሐሳብመሪነት ፣ጥበበኝነት ፣ተባባሪነት፣አርአያነት፣ታዛዥነት፣እና ተጠያቂነት ናቸው፡፡</p>

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት የተመሰረተው ጥቅምት 4 ቀን 1959 ዓ.ም ሲሆን በጊዜው የነበረው ስያሜ የብስራተ ገብርኤል ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር የሚል ነበር ፡፡ የመጀመሪያ ዓላማው “ሰው በእህል ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ” ማቴ 4 ÷ 4 ተብሎ በቅዱስ መፅሐፍ እንደተነገረው ቃለ እግዚአብሔር ምግበ ነፍስ ምግበ ስጋ እንደመሆኑ መጠን በዕለተ ሰንበት የሰንበት ትምህርት ከሚያስፈልጋቸው ተገልጋዮች መካከል ወጣቶችንና ሕፃናትን ለማስተማር ነበር፡፡ ማህበሩ እስከ 1968 ዓ.ም ድረስ የተለያዩ ፈተናዎችን በማሳለፍ 24 አንቀፅ የያዘ የመተዳደሪያ ደንብ በማርቀቅ ሚያዚያ 16 ቀን 1968 ዓ.ም&nbsp; አንዲመራ በማድረግ ግንቦት 28 1968 ዓ.ም አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ተመሰረተ፡፡

ስለ እኛ

ሰንበት ትምህርት ቤቱ 10 ዋና ዋና ክፍላትና 35 ንዑስ ክፍላትን (የስራ ቡድኖች) በመያዝ የተለያዩ የሰንብት ትምህርት ቤት አገለግሎቶች ይሰጣል፡፡

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

ስለ ቤተክርስቲያኑ ታሪክ እና መግለጫ

የደብረ ብስራተ ቅዱስ ገብርኤል ፅላት አመጣጥ ታሪክ የሚጀምረው በ1869 ዓ.ም አቶ ቡሌ ወይም አቶ ቡቱ ቡኬ ለሚባሉ አረኛ በአሁኑ ድል ገበያ በድሮ የመን ኤምባሲ አካባቢ ተገልጾላቸው ነው፡፡ የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ታህሳስ 22 ቀን 1954 ዓ.ም እንዲከበር በተደረገበት ወቅት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በተገኙበት ሦስት ድንኳኖች ተጥለው የብስራተ ገብርኤል በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲከበር ተደረገ ፡፡ ታቦቱም ጸበሉ ያለበት ቦታ እንዲያርፍ ተደረገ፡፡ አሁን ያለበትም ቦታ ላይ የመሰረተ ድንጋይ ተጣለ፡፡

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251911683572

ኢሜል

anketsebitsuan@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

8 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

Debre Bisrat Kidus Gebriel Church

Address

8 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

Lat 8.99113Lng 38.72690
Open in Google Maps