በክፍለ ከተማቸን የሚገኙ ሰ/ት/ቤቶቸ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ የሥራ አመራር መርጫ እያከናወኑ ይገኛሉ
በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሥር ከሚገኙ ከ/ክተሞች አንድነት አንዱ በሆነው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ በ13/10/2018ዓ.ም እና እሑድ በ14/10/2018 ዓ.ም 5(አምስት) አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ሥራ አመራር ምርጫ አከናውነዋል። 1.ቂሊንጦ መካነ ፍስሃ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት 2. አቃቂ መካና ደብረ ብስራት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት 3.ቱሉ ዲምቱ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤልቤ/ክ ሰ/ት/ቤት 4.ሐመረ ወርቅ ቅ/ማርያም እና ቅድስት አረሴማ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት 5. ሳሪስ ዳማ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት ሲሆኑ 📌በአጠቃላይ እንደ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ከሃያ ሰባቱ (27) አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች 12ቱ በአንድነቱ መመሪያ መሠረት በአግባቡ የመረጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ሰ/ት/ቤቶች በሙሉ እስከ ሰኔ 28/2018 ዓ.ም መርጠው የሚያጠናቅቁ ይሆናል።