Sunday SchoolActive

የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል

Gofa Beza Bizuhan St. Kidane Mihret Cathedral

መዝገበ ምሕረት ሰንበት ትምህርት ቤት

ሰ/ት/ቤት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው  እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት የትምህርት ቦታ ነች፡፡ ቤተክርስቲያናችን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት ስታካሒድ ኖራለች፤ ሰ/ት/ቤታችንም ከተመሠረ

05 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ
1991 ዓ.ም
+251993647953
Gofa Beza Bizuhan St. Kidane Mihret Cathedral
Gofa Beza Bizuhan St. Kidane Mihret Cathedral

Sunday School

Gofa Beza Bizuhan St. Kidane Mihret Cathedral

05 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

ቤተ ክርስቲያናት

Churches

Latest updates

አዳዲስ መረጃዎች እና ብሎጎች

በጣም ቅርብ ጊዜ የተጨመሩ ጽሑፎችን እና መርሃ ግብሮችን በተመረጠ አቀራረብ ይመልከቱ።

የእኛ ተልእኮ፣ ራእይ እና ዓላማ

የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል ለማህበረሰቡ የሚያቀርበውን የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አላማ ከታች በግልፅ መልኩ አቀርበናል።

የእኛ ተልእኮ

<p>በማቴ 28፥19 “እንግዲህ ሂዱና በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፡፡” የሚለውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ትምህርተ ወንጌልን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለሕፃናት፣ ለወጣቶች እንዲሁም ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ተተኪዎችን ማፍራት ነው፡፡</p>

የእኛ ራእይ

<p>የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትና የአጥቢያው ምዕመናን፤ የቤተክስቲያንን መሠረተ እምነት (ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት) የተገነዘቡ፣ በሕይወታቸው አርአያ የሚሆኑ፣ ዓለም አቀፋዊና አካባቢያዊ ለውጦችን የተረዱና በኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ የተቃኙ፣ለቤተክርስቲያንና ለሀገር የተሻለ ሥራ የሚሠሩ ዜጎች ሆነው ማየት፡፡</p>

የእኛ እሴቶች

<p>እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሰውን ማክበር፣ በፍቅር የሆነ አገልግሎት፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ፣ ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት ፣ ጽናትና ምስክርነት ፣ ዘመኑን መቅደም መዋጀት</p>

ስለ ሰንበት ት/ቤቱ

ለሁሉም እድሜ ደረጃ እምነት፣ ትምህርት እና አስተባበር ማሳደግ

የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል

መዝገበ ምሕረት ሰንበት ትምህርት ቤት

ስለ አመሰራረቱ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት በአብነት ትምህርት ቤቶች ተማሪ ቁጥር እንዲቀንስ አደረገ። ሚሲዮናውያን ወጣቶችን ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው ለማራቅ ሲንቀሳቀሱ፣ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ደግሞ የራስ ማንነትን የመጠበቅ ስሜት ፈጠረ። በዚህ ምክንያት በ1936 ዓ.ም. በፈቃደኛ ወጣቶችና ካህናት አነሳሽነት የቅዳሜና እሑድ ትምህርት ቤቶች ተቋቋሙ። በ1970 ዓ.ም. ሰንበት ትምህርት ቤቶች በቃለ ዐዋዲ እውቅና ተሰጣቸው። ሰ/ት/ቤታችን በ ሐምሌ 14 ቀን 1983 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡

ስለ እኛ

ሰ/ት/ቤት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና በአመቺ ጊዜ ሁሉ በየአጥቢያው  እየተገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዐት ምግባር የሚያጠኑበት የትምህርት ቦታ ነች፡፡ ቤተክርስቲያናችን በጉዞዋ ሁሉ ሕፃናቱን፣ ወጣቱን፣ ጎልማሳው እና አረጋዊያንን በማጣመር መንፈሳዊና ሀገራዊ ልማት ስታካሒድ ኖራለች፤ ሰ/ት/ቤታችንም ከተመሠረተበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ዘርፍ ወጣቱን ከሕፃንነቱ ጀምሮ በማስተማር ለሰው ልጅ በሚያፈልጉት የአአምሮና የመንፈስ እድገት የተሟላ እንዲሆኑ ስትሠራ በተጨማሪም ማኅበራዊ ግዴታዎቿን በመወጣት ላይ ትገኛለች፡፡ 

የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

No services available.

Please check back later for updated service information.

ያግኙን

የሰንበት ትምህርትቤቶች አንድነትን ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያሉትን አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ

ስልክ

+251993647953

ኢሜል

mezgebe.meheret@gmail.com

ሁኔታ

Active

አድራሻ

05 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እና አስተያየት ከታች ያለውን ፎርም ይጠቀሙ

Location

አካባቢ

Gofa Beza Bizuhan St. Kidane Mihret Cathedral

Address

05 • ንፋስ ስልክ ላፍቶ • አዲስ አበባ

Lat 8.97194Lng 38.73409
Open in Google Maps